እውነታው ይኽው ነው!


1.የኦሮሞ ህዝብ በቋንቋው የመዳኘት ፣ የመማር ፣ የህክምና አገልግሎት እና መንፈሳዊ አገልግሎት የማግኘት ለምዕተ ዓመት የታገለለት ጥያቄ ነው። ይህን ጥያቄውን መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ያሉት ልጆቹ ጥያቄህ ጥያቄያችን ነው ብለው ሲያነሱ እና ሲታገሉለት ከሰው በላ ስርዓት ተከላክሎአቸው ለክብር አብቅቶአቸዋል። እነ ዶክተር አቢይ የዛሬ ስድስት ሰባት ዓመት የህዝቡን ጥያቄ ሲያነሱ ህዝቡ ለነጌታቸው አሰፋ የአፈና መዋቅር አሳልፎ አልሰጣቸውም። ይልቂዬ ለትልቅ ክብር አብቅቶአቸዋል።
ዛሬም የኦሮሞ ህዝብ ለምዕተ ዓመት ሲያቀነቅን የነበረውን ፍትሃዊ ጥያቄውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የስልጣን ተዋረድ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ልጆቹ ሲያነሱ ለአነ አቡነ አብረሃም የአፈና መዋቅር አሳልፎ አይሰጣቸውም። አብሮአቸው ይቆማል።የሚገባቸውንም ክብር ይሰጣቸዋል።
ለዚህ ደግሞ ታሪክ ምስክር ነው።
2. የኦሮሞ ህዝብ ለኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት እውቅና መስጠት ብቻም ሳይሆን በትግሉ እና በመሰዋዓትናት ያፀናው መዋቅር ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የበላይ አመራር ግን ይህንን የህዝቡን ፍላጎት እና ህዝቡ በትግሉ ያፀናውን ክልሉን እውቅና ነስቶት ቆይቷል። ህዝቡ ይህንን አግባብ ያልሆነ አካሄድ እና አመለካከት የቤተክርቲያኗ አመራር እንዲያስተካክል ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ እና በጎ ምላሽ ለማግኘት በትግስት ሲጣብቅ ነበር።
አሁን ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የስልጣን ተዋረድ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ጳጳሳት ይህንን የረጅም ጊዜ የህዝቡ ጥያቄ የሆነውን ለክልሉ እውቅና ሰጥተን ከክልሉ ጋር በመስራት የቤተ እምናቷን እና የአማኙን መብት እናስከብር ብለው በመጠየቃቸው መልሱ ውግዘት ከሆነ የኦሮሞ ህዝብ የሚያከብረውን ያከበሩለትን ያከብራል። አብሮዓቸውም ይቆማል። የህዝቡን ጥያቄ ጥያቄያቸው በማድረግ መስዋዓትነት ከከፈሉት ጋር አብሮ ይቆማል።
ለዚህ ደግሞ ታሪክ ምስክር ነው።
3. እነ አቡነ ሳዊሮስ ያነሱት ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከመቆርቆር ፣ በኦሮሚያ እና በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዋች ያሉት አማኞች የቤተክርትያኗ ጥቂት አባቶች በሚከተሉት ፀረ ብዙሃንነት አማኙ ሸሽቶናል ። በአገልጋዮች እጥረት በየገጠሩ ብዙ ቤተዕምነቶች ተዘግተዋል። ስለዚህ የህዝቡን ቋንቋ እና ባህል የሚያውቁ አገልጋዮች ይመደቡልን ነው።
ይህንን በየገጠሩ ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ እምነት ተከታዮች የሚያውቅቱ ሃቅ ነው። ይህንን የአደባባይ ምስጥር በጥያቄ መልክ ያቀረቡት አባቶች ያቀረቡት አማኙን እና ቤተክርስቲያናቸውን በማክበር ነው።ለአማኙ እና ለቤተዕምነቷ ጥቅም ነው። ለዚህ እነ አቡነ አብረሃም የሰጡት መልስ ማውገዝ ከሆነ እውናቱን የሚያውቀው አማኝ ተቃራኒውን ያደርጋል። አማኙን እና ቤተዕምነታቸውን አክብረው ጥያቄውን ያነሱትን አባቶች ያክብራል።
ለዚህ ደግሞ ታሪክ ምስክር ነው።
4.አንዳንድ ዩቱበሮች እንደ እነ ደረጀ ሃብተወልድ ዓይነት ሕዝብ በሕዝብ ላይ እንዲነሳ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ የማይታወቅ እንዳይመስላችሁ፤ኦሮሞም ሆነ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች በቋንቋችን የእምነትን አስተምህሮ እንወቅ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትን እናጠናክር ብለው ፍትሃዊ ጥያቄ በማቅረባቸው የሚኮነኑበት ተጨባጭ ምክንያት ሊኖር አይችልም
5.መንግስት በጉዳዩ እንዲገባ በመገፋፋት ላይ የምትገኙ በተለይም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና አቶ ሽመልስ አብዲሳን ስም በመጥቀስ ተገቢ ያልሆነ ነገር በመናገር ላይ የምትገኙ ወገኖች እረፉ! ትክክል አይደላችሁም #Ethiopia
No photo description available.
Like
Comment
Share

Post a Comment

0 Comments