የ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጠናቋል

 


የ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም ተጠናቋል፤የትዊተር አርበኛ አፍሯል ውርደቱን ተከናንቧል

ይህን ተከትሎ የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት መሪዎች ትናንት ምሽቱን ወደ አገራቸው መመለስ ጀምረዋል። 

እስካሁን የበርካታ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

እስካሁን ድረስ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት መካከል ፦

- የጋና፣

- የሞዛምቢክ፣ 

- የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ 

- የኬኒያ፣ 

- የሩዋንዳ፣ 

- የሞሮኮ፣ 

- የማዳጋስካር ፣ 

- የኡጋንዳ፣ 

- የዚምባብዌ ፣ 

- አንጎላ ፣

- ደቡብ አፍሪካ ፣

- ኮንጎ ብራዛቢል፣

- ቻድ እንዲሁም የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ መሪዎች ይጠቀሳሉ።

የተመድ ዋና ፀሀፊት አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ ሌሎችም የጉባኤው ተካፋዮች ተሸኝተዋል።

መሪዎቹ ትላንትናና ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ከመሳተፍ ባለፈ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። 

በሌላ በኩል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ባለድርሻ አካላትንም አመስግነዋል አቅርበዋል።

Post a Comment

0 Comments