የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ጨፌ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፤እስከ ነገው ቅዳሜ የካቲት 11 2015 ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል
ዛሬ ጠዋት በተጀመረው የጨፌ ጉባኤ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉን መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በንባብ ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸው የክልሉ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች እንቅስቃሴ ጠምንካራና በክፍተት ያጋጠሙ ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል
እንዲሁም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርትቸው ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የ " ኦነግ ሸኔ " ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ በድጋሜ አቅርበዋል
የጨፌው አባላት በቀረበላቸው ሪፖርት ላይ በመወያየት ላይ ይገኛሉ፤በጉባኤው ላይ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ሹመቶች ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሏል
በጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ይፀድቃሉ ተብሎ የሚጠበቁ ረቂቅ አዋጆች
1.ተሻሽሎ የቀረበ የገጠር መሬት አስተዳዳርና አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ
2.የኦሮሚያ ኢንቬስርመንት ስራ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ
3.ተሻሽሎ የቀረበ የኦሮሚያ ከተሞች ምስረታ ምስረታ ረቂቅ አዋጅ
4.ተሻሽሎ የቀረበ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ አደረጃጀት ስልጣንና ኃላፊነት ረቂቅ አዋጅ ሲሆኑ የተለያዩ ሹመቶችም ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል
0 Comments