ፊንፊኔ
#Ethiopia የካቲት 17,2015(YMN)
ለቦረና ዞን የድርቅ አደጋ ተጎጂ ወገኖች አዛኝ ቅቤ አንጓቾች ብቅ ብቅ ማለታቸው ታይቷል መልካም ነው ‘ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም”
ነውና እዝነታቸው ከልብ ከሆነ የእርዳታ እጃቸውን ይዘርጉ፤ካለበለዚያ የተለመደ ጩኸታቸውን ያቁሙ!
በወገኖች ጉዳት የፖለቲካ ትርፍን ለማጋበስ መሯሯጥ የትም ሊያደርስ አይችልም፤ትዝብት ውስጥም ይጥላል፤እያየን
ያለነው የአዛኝ ቅቤ አንጓቾችን ሩጫ ነው
የቦረና ሕዝብ ለድርቅ አደጋ የተጋለጠው ዘንድሮ ብቻ አይደለም የአየር ንብረት ለውጥ ችግር አካባቢውን
ለተደጋጋሚ ጊዜ ጎድቶታል በአደጋው ምክንያት በሚሊየን የሚቀጠሩ የቀንድ ከብቶች አልቀዋል የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ መንግስት
የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው
ለመሆኑ አዛኝ
ቅቤ አንጓቾቹ መንግስት ላይ ጣት ከመቀሰር በፊት አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ሚናቸውን
መወጣት አለመወጣታቸውን ጠይቀዋል?መንግስት የበዛበትን ፈተና ተቋሞም ቢሆን የሚጠበቅበትን ሲያደርግ እንደነበርና
አሁንም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ መቼም ይታወቃል
እኛ በበኩላችን ለቦረና ህዝብ
ማድረግ ያለብንን እናድርግ እንጂ ለፖለቲካ ትርፍ
ሲባል መንግስት ላይ ጣት መቀሰር በድርቅ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ምን ዓይነት ጥቅም ያመጣል?እንጠይቅ! ልክ እንደተለመደው የኦሮሚያ
ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ወይም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ግፊት በማድረግ በዚህ
ምክንያት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ተፈልጎ ይሆን?
በየትኛውም
አጋጣሚና ሁኔታ መጠቀምን የሚያውቁበት ኃይሎች የቦረናን ድርቅ ለዓላማቸው ከግብ መድረስ ሊያግዘን ይችላል በሚል ከንቱ ተስፋ የመንግስት
ባለስለጣናት ላይ ጣታቸውን በመቀሰር ላይ ይገኛሉ
ሲያምራቸው
ይቀራል እንጂ በሰበስ አስባቡ እየተሽሎኮሎኩ ሌት ተቀን የሚመኟትን ስልጣን የሚፈናጠጡበት ሁኔታ በፍፁም የለም! እንደተለመደው ወገን
ለወገን ይደርሳል፤የቦረና ሕዝብም ካጋጠመው አስከፊ የድርቅ አደጋ ይወጣል
የቦረና ዞን እንስሳት ሃብት ወደፊት ሊተካ የሚችል ነው
ሊተካ የማይችለውን የሰው ሕይወት ከሞት ማትረፍ ጊዜ የሚይሰጠው ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ወገን ሊረባረብ ይገባል! ከዚህ ውጭ ያለው
ጩኸት ትርፍ ነው ምንም ጥቅም የለውም ባዶ!
0 Comments