ጽንፈኞች መንግስት ለመገልበጥ ያዘጋጁት ስትራቴጂ ቁጥር ሦስት(3)




ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 14,2015(YMN) ጽንፈኞች የኢትዮጰያን መንግስት ለመገልበጥ ያግዘናል ብለው ካዘጋጁት ስትራቴጂ ውስጥ አንዱ ፊንፊኔ/አዲስ አበባን የግጭት ማቀጣጠያ ማዕከል ማድረግ ነው፤በክፍል ሁለት ጽሑፌ ጽንፈኞች የዜጎችን መፈናቀል ለፖለቲካ ንግድ በማዋል እንዴት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ማሳያዎችን በመጠቆም አቅርቤ ነበር፤በመቀጠል ጽንፈኞች ፊንፊኔ/አዲስ አበባን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ስትራቴጂ አዘጋጅተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙበትን ሁኔታ አቀርባለሁ መልካም ንባብ!

ስትራቴጂ 3: ፊንፊኔ/አዲስ አበባን የግጭት ማዕከል ማድረግ

ፊንፊኔ የአገራንችን ዋነኛ የፖለቲካ ማዕከል ናት፤የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት መቀመጫ እንዲሁም የአፍሪካ አህጉርና የዓለም አቀፍ ተቋማት ማዕከል መሆኗ ይታወቃል፤ጽንፈኞች ተሰሚነትን ለማግኘት ሲሉ በተለያዩ ወቅቶች ፊንፊኔ ላይ ትኩረት በማድረግ ተደጋጋሚ ያልተሳካ የብጥብጥ ሙከራዎችን አድርገዋል

በቅርቡም በለመዱት አካሄድ የብጥብጥ ዕቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ቢንፈራገጡም ከግባቸው መድረስ አልቻሉም፤ያሰቡት ሳይሳካ ቀረ፤የተዘጋጁበት ዕቅድ ከሸፈ

የካቲት 23,2015 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ፊንፊኔ ውስጥ ታስቦ ከዋለው 127ኛ የአድዋ ድል በዓል ጋር በተያያዘ የተዘጋጁበትና ተግባራዊ ለማድረግ ያቀዱት የብጥብጥ ዕቅድ በፀጥታ ተቋማት ብቃት ከሸፈባቸው፤ይህ የድል መታሰቢያ ቀን በሚኒሊክ አደባባይ መከበር አለበት እንጂ ለምን ወደ መስቀል አደባባይ ይወሰዳል?መከላከያ ሠራዊት በዓሉን የማስተባበር ኃላፈነት ለምን ተሰጠው?ብለው በመቃወም በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የፈፀሙትን አስነዋሪ ድርጊት ማስታወስ ተገቢ ነው

ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመደበቅ በፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ላይ ድንጋይ በመወርወር ብጥብጥ እንዲቀጣጠልና በዚህም ምክንያት የአንድ ሰው ሕይወት እንዲያልፍና የተወሰኑ ሰዎችም ለአካል ጉዳት እንዲጋለጡ አድርገዋል፤በወቅቱ በነበረው ሁኔታ የፖሊስ ኃይል አስለቃሽ ጭስ ለመርጨት የተገደደ በመሆኑ በርካታ ሰዎች እንዲጎዱ አድርገዋል

ቀደም ሲልም በሃይማኖት አባቶች አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረውን ሁኔታ ተገን በማድረግ ያልተፈቀደ ሰልፍ የካቲት 5,2015 ዓ.ም ካልወጣን ብለው በማስቸገር የሚመለከተው የመንግስት አካል ባለመፍቀዱ እንዲቀር ተደርጓል፤የአድዋ ድል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት የየካቲት አምስቱ ዕቅድ የተደናቀፈ በመሆኑ በቁጭት የተፈፀመ ነው ማለት ይቻላል

ጽንፈኞች ባገኙት ምቹ ሁኔታ ሁሉ በመጠቀም ፊንፊኔን የብጥብጥ ማዕከል ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይሉ በተለያዩ ወቅቶች ያደረጉት ጥረት ተጨባጭ ማሳያ ነው፤ወደፊትም የለመዱትን እኩይ ድርጊት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይሉ ይታወቃል

በውጭ አገር የሚገኙ የጽንፈኛ ቡድኖች አስተባባሪዎች እንደ ታማኝ በየነ ያሉቱ”የአብይን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ፤ለመገልበጥ አንድ መቶ ሺህ ሰው ብቻ የሚሳተፍ ሰልፍ ይበቃል” በማለት ያስተላለፈውን መመሪያ  ተግባራዊ ለማድረግ ጽንፈኞች ተጠራርተው ፊንፊኔን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ቢፍጨረጨሩም የጠበቁትን ውጤት ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል

ከዚህ ሌላ ጽንፈኛ ሃይሎች በርካታ ያዘጋጇቸው ሰዎች ከአማራ ክልል፤ከደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች ወደ ፊንፊኔ እንዲመጡ በማድረግ ፊንፊኔን የግጭት ማዕከል ለማድረግ ብርቱ ጥረት አድርገዋል፤በተለይም በርካታ ወጣቶች ከአማራ ክልል ወደ ፊንፊኔ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተረጋግጧል መንግስት ይህን የጽንፈኞች ሴራ ቀድሞ በመረዳቱ በርካታ ሰዎች ወደ ፊንፊኔ የሚያደርጉት ጉዞ እንዲገደብ አድርጎ ነበር በወቅቱ ትክክለኛ እርምጃ ነው የተወሰደው

መንግስት ለጥንቀቄ ብሎ በወሰደው እርምጃ ላይም ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ዜጎች መንግስትን እንዲጠራጠሩና ጥላቻ ውስጥ እንዲገቡ ተሰርቷል፤ጽንፈኞች የተዘጋጁበትን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ በአገኙት የተኛውም አጋጣሚ እንደሚጠቀሙ ታውቋል፤እንደ ፍላጎትና ጥረታቸው ቢሆንማ ኖሮ ፊንፊኔ የግጭት ማዕከል ሆና የመንግስት ግልበጣ ቅዠታቸው ይሳካ ነበር ይህ ጽሑፉን የምታነቡለት ሰውዬፍም አይኖርም ቢኖርም እንዲህ መፃፍ አይችልም!ግን የታሰበው አልሆነም ከሽፎ ቀረ እነሱም እፍረታቸውን ለመከናነብ ተገደዱ

ጽንፈኞችን ከሚደግፉ ጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው የፊንፊኔ ነዋሪ ጥሮ ግሮ ሕይወቱን መምራት የሚፈልግ ነው አብዛኛው ነዋሪ ለብጥብጥ የሚተርፈው ጊዜ እንኳ የለውም በሰላም ወጥቶ ሰርቶ በሰላም ወደ ቤቱ መመለስ የሚሻ ነው፤ጽንፈኛ ቡድኖች ግን የኑሮ ውድነት ችግር እንዲፈጠር በማድረግ ጭምር በሰላም መኖር የሚፈልጉ ዜጎች እንዳይረጋጉ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጨባጩን ሁኔታ በመረዳት የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል የዋጋ ንረት ሴራ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ የምርት አቅርቦት እንዲጨምር በማድረግ ህብረተሰቡ እንዲረጋጋ በማድረግ ላይ ይገኛል፤ይህ የመንግስት እርምጃ የፊንፊኔ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ዘላቂ ማድረግ በሚያስችል መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፤አብዛኛው ነዋሪ ለኑሮ ውድነት ችግር ሲጋለጥ ለጽንፈኛ ቡድኖች ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር ስለሆነ የትኛውም ጽንፈኛ ሃይል ምቹ ሁኔታ እንዳያገኝ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት መስራት ጽንፈኞች ፊንፊኔን የግጭት ማዕከል እንዳያደርጉ መስራት የሁሉም ግዴታ ነው

 

 

 

Post a Comment

0 Comments