እንዲህ ሆነ



ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በማጥላላትና በማንጓጠጥ ጌታቸው ረዳን የሚወዳደር ያለ አይመስለኝም።እነሀብታሙ አያሌውና ኤርሚያስ ለገሰ የእሱ ደቀመዛሙርት እንጂ ተወዳዳሪው አይሆኑም።ዛሬ ሊጠቀስ ከሚያሳፍረው ስድብና ዘለፋም አልፎ "...ጦርነቱ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ...ሳዳም ሁሴንም ሆነ ኤርዶጋን አያድኑትም...የትም ቢገባ ጉሮሮውን አንቀን ለፍርድ እናቀርበዋለን..."እስከማለት የደረሰ ዛቻና ፉከራ አሰማ።ጌታቸው ረዳ መግለጫ በሰጠ ቁጥር የንግግሩ መጀመሪያ"ፋሽስቱን"አብይ አህመድ መዝለፍ ነበር።ጠ/ሚር አብይ አህመድ የጌታቸው ረዳን ስድብ÷ማራከስና ፉከራ አልሰሙም ማለት አይቻልም።ሆኖም ያንን ክብር አዋራጅና ተሳዳቢ ጌታቸው ረዳን የትግራይ የሽግግር አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾሙት።ቂም በቀል ባህል በሆነበትና "ከዘመናት በፊት ተፈፀመ"የሚባል የቂም በቀል ትርክት በሚሰበክበት ኢትዮጵያ ተሳዳቢውንና ክብር አዋራጁንጌታቸው ረዳ ሹመውታል።ቂም በቀል እንደባቄላ በሚቆረጠምበት አገር እንዲህ ዓይነት ፖለቲካዊ ውሳኔ አስገራሚና አስደማሚ ነው።ተወደደም ተጠላም የዶ/ር አብይን የሞራል ልዕልና÷ይቅር ባይነትና ለነገው ትውልድ አሳቢነት ማድነቅ ግድ ነው።ቂም በቀልን ለሚቆረጥመው የጥላቻ ኃይልም መራራ ትምህርት ነው።ኢትዮጵያ የምትፈልገው እንዲህ ዓይነት ይቅርባይ መሪዎችን ነው።አይናችን እያዬ ጆሮአችን እየሰማ የሆነው ይህ ነው።ከዚህ ይቅርባይነትና የሞራል ልዕልና በስተጀርባ የነገ ፖለቲካዊ ቢሆን/political cenarios) መኖሩን ካልገመትክ ቁሞ ቀር ሆነኃል ማለት ነው።የፈለከውን የስድብ ናዳ አውርድ እንጂ "የመደመር ትውልድ"አርአያና መሪ ዶ/ር አብይ አህመድ ነው ብዬ አምናለሁ።

(ዓለምነው አበበ)

Post a Comment

0 Comments