አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አልሳቱም!





ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 15,2015(YMN) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሰሞኑን በተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር ምክንያት ተነካን ያሉ የአማራ ጽንፈኞች ኡኡታን እየተመለከትን ነው

አምባሳደሩ ከተናገሯቸው እውነቶች ውስጥ አንዱን በመምዘዝ በጦር መሳሪያ ጉዳይ ላይ  የተናገሩትን እውነት ብቻ እንይ! ፅንፈኞችን እያንገበገበ ያለው አምባሳደሩ የጦር መሳሪያን ጉዳይ አንስተው ያለውን ተጨባጭ እውነት መናገራቸው ነው፤በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድና ዝውውር የከበሩ ፅንፈኞችና ጀሌዎቻቸው እሪ ብለው በመጮህ ላይ የሚገኙት የለመዱት ጥቅም እንዳይቀርባቸው በመስጋት ነው

ባገኘው ምቹ አጋጣሚ ሁሉ በጦር መሳሪያ ዜጎችን በማስፈራራት ዝርፊያ የለመደ ኃይል ትጥቅህን አስቀምጥ ወይም አስረክብ ሲባል ደስተኛ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም፤ምክንያቱም ይህን ካደረገ የለመደው ጥቅም ይቋረጥበታል፤የህግ የበላይነት ከተረጋገጠ ሽፍታ በጦር መሳሪያ በማስፈራራት እንደፈላጎቱ መዝረፍ አይችልም

በጦር መሳሪያ ንግድና ዝውውር ላይ በመንግስት የሚደረገው ጠንካራ ቁጥጥር ጥቅመኞች በጦር መሳሪያ ንግድና ዝውውር የሚያገኙትን ገቢ የሚያስቀርባቸው ነው፤ስለዚህ መጮኻቸውና ኡኡታቸውን ማቅለጣቸው የሚጠበቅ ነው

ይህ ከውስጥና ከውጭ የተቀናጀ ጽንፈኛ ኃይል ያለ ምክንያት እየጮኸ እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፤በመሳሪያ ኃይል ተጠቅሞ ስልጣንን በጉልበት ለመንጠቅ ያደረገው ቅድመ ዝግጅት ከግቡ ሳይደርስ ስለሚከሽፍበት የተነገረውን እውነት በመንጫጫትና በጩኸት ለማፈን ሲል በግለሰቡ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ከፍቶ በመረባረብ ላይ ይገኛል

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሁለት ዓመታት በፊት በሕወሃት ላይ ተወስኖ የነበረው የሽብርተኝነት ስያሜ መነሳቱም የአማራ ጽንፈኞችን ባልተጠበቀ ሁኔታ አስቆጥቷል፤ከነበረው አጠቃላይ ሁኔታ በመነሳት ይህን ውሳኔ በቅንነት የሚቃወሙ ዜጎች አሉ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሽብርተኝነት ስያሜው መነሳቱን በመልካምነት የማይመለከቱ ወገኖች ተጨባጩን እውነታ ባለመረዳታቸው ምክንያት ስለሆነ በማስረዳትና እውነታውን በመንገር እንዲታረሙ ማድረግ ይቻላል መንግስት ዜጎች እውነቱን እንዲረዱ መስራት ይጠበቅበታል፤ሚዲያዎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ቢሰሩ መልካም ነው

በእርግጥ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ላይ ያካሄዱት ውይይት በሚዲያ ለሕዝብ መቅረቡ መልካም ነው፤ውይይቱ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያግዝ ነው አሳሳቢው ጉዳይ ስንቱ ሰው ሚዲያውን በጥሞና ይከታተላል?የሚል ነው፤ስለዚህ ተጨማሪ ስራዎች መከናወን አለባቸው ምሁራን፤ የሕግ ባለሙያዎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ይህ መሆን ያለበት በቅንነት የተሳሳተ አቋም የያዙ ዜጎች መታረም እንዲችሉ ነው

“አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም” እንደሚባለው ጽንፈኞቹ ለጥቅማቸው ሲሉ በማደናገር ላይ የሚገኙ ስለሆነ እነርሱን ለመለወጥ መሞከር ድንጋይ ላይ ውሃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል እነርሱን መተው ነው የሚሻለው እንደለመዱት ይጩኹ!ሌላ አጀንዳ እስኪያገኙ ድረስ ይህንኑ እያመነዠኩ መሰንበታቸው አይቀርም

 

Post a Comment

0 Comments