መማሪያ



ብዙ የፖለቲካና የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን አጥንተውም ሆነ ገልጸው ካልጨረሷቸው የጥናት ዘርፎች አንዱ ፖለቲከኞች ለምን የፖለቲካ ስልጣን ርሀብተኛና ስስታም እንደሆኑ (Why are so many politicians greedy and power hungry?) ማወቅን የሚመለከተው ነው፡፡ምሁራኑ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች ታሪክ ቢሰሙና ቢመለከቱ መገረማቸው የማይቀር ይመስለኛል፡፡እንደኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የስልጣን ርሀብተኛና ስስታም አለመኖሩን ለማወቅ ባለፉት ቅርብ ዓመታት የተመዘገበውን ሁነት ብቻ መገንዘብ በቂ ነው፡፡በኢትዮጵያ የስልጣን ርሀብተኝነትና ስስታምነት ምክንያት በነጭና ቀይ ሽብር ያለቀውን ወጣት ትውልድ ማሰብ ነው፡፡እሱም በቂ አይደለም፡፡በአማጺነትና በሽምቅ ተዋጊነት የረገፈ የሰው ህይወትና የወደመ የሀገር ሀብት ተቆጥሮም ተሰልቶም የሚያልቅ አይደለም፡፡አሳሳዛኙ ነገር ለስልጣን ርሀብተኝነትና ስስታምነት የተሰጠው የክርስትና ስም ‘’ለህዝብ መብትና ነጻነት መታገል ‘’የሚል ነው፡፡ በዚየስልጣን ርሀብተኝነትና ስስታምነት ደግሞ እንደ ህወኃት በግንባርቀደምትነት የሚጠቀስ የለም፡፡ህዝብ ፈጅቶና አስፈጅቶ ስልጣን ከያዘ ከ27 ዓመታት በኋላ ‘’ህዝብንና አገርን ስለበደልክ ስልጣኑ በቃህ ‘’ሲባል ተሰበባስቦ ወደ መነሻ ቦታው ትግራይ ገባና የተለመደውን ‘’ለትግራይ ህዝብ መብትና ነጻነት መታገል ‘’ካባ ለብሶ በቀሰቀሰው ጦርነት ትግራይን ወጣት አልባ አደረገ፡፡በስልጣን ስግብግብነቱ ምክንያት ትግራይን ወደ ድንጋይ ዘመንነት መለሰ፡፡በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠር የትግራይ ወጣትና አዛውንትን አስፈጅቶ ከጨረሰ በኋላ ወደ ስልጣን እንደሚመለስ ተስፋ አደረገ፡፡ይህን ታዳጊ ተመልከቱት፡፡በህወኃት የስልጣን ስግብግብነት ምክንያት የተከፈተ ጦርነት ሰለባ ነው፡፡በዚህ ለጋ ዕድሜው ት/ቤት መዋል፣ለመጭው ብሩህ ህይወቱ ዕውቀት ማካበት ሲገባው ‘’ለትግራ ህዝብ መብትና ነጻነት መታገል አለብህ ‘’ተብሎ ለእሳት ተማገደ፡፡እሱ ሁለት እግሮቹን አጥቶ በህይወት ቢተርፍም ሌሎች ዕልፍ አዕላፍ ጓደኞቹ ግን በየሜዳና ተራራው እንደቅል ረግፈው ቀርተዋል፡፡እጅና እግሩን የገበረው ለነደብረጽንና ለነጌታቸው ረዳ የስልጣን ስስታምነት እንደሆነ ዛሬ ሳይገባው አይቀርም፡፡ትግራይና ወጣቶቿ የዚህ ዘመን የህወኃት የስልጣን ርሀብተኞችና ስስታሞቸ ሰለባ መሆናቸው አንገት ያስደፋል፡፡የፖለቲካና ማህበረራዊ ሳይንስ ምሁራን ይህን ጉድ ቢያጠኑት ከህወኃት ተፈጥሮና ባህሪ ዓለም የሚማርበት መጽፍ (Text Book) ማግኘታቸው አይቀርም፡፡አሳዛኝ ትውልድ!!

(በዓለምነው አበበ)

Post a Comment

0 Comments