በአሁኗ ኢትዮጵያ የተንገሸገሹቱ እውነታውን ሊረዱ ይገባል!

  

 


በውጭ የሚገኘው ጽንፈኛው ኃይል ፕሮፓጋንዲስቶች ውስጥ  ደረጀ ሃብተወልደ እና መሳይ መኮንን ጥቂቶቹ ናቸው

ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 11,2015(YMN) የአማራ ጽንፈኞች በአሁኗ ኢትዮጵያ ደስተኛ አለመሆናቸውን በተግባራቻው እያሳዩ ነው፤እነርሱ የሌሉበት ኢትዮጵያ እንደማትጥማቸው፤እንደምታንገሸግሻቸው አይተናል ሰምተናል

እንግዲህ ምን ይደረግ?ጽንፈኞች አጥብቀው የሚሿት የጥንቷ ኢትዮጵያ ልትመለስ አትችልም ስለዚህ አዋጩ መንገድ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ከመንጨርጨር ይልቅ አዲስቷን ኢትዮጵያ በመቀበል በአዲስቷ ኢትዮጵያ ሕግና ስርዓት መሰረት መኖር ብቻ ነው፤ባዶ ሜዳ ላይ እያየን ባለው ፉከራና ቀረርቶ ጠብ የሚል ነገር የለም

ጽንፈኞች ሁሉንም ነገር ክደው ይነሳሉ ምክንያቱም የጥንት አያትና አባቶቻቸው ሲከተሉ የነበሩት የእኛ እናውቅልሃልን መርህ አሁን ሊሰራ የማይችል መሆኑን ሊረዱ የሚችሉበት አዕምሮ የላቸውም

የሚያስብ ፍጡር ቢያንስ በሌላው ዘንድም ተቀባይነት ለማግኘት ሲል ሚዛናዊ አቀራረብን ይከተላል እነዚህ ደረቅ ስለሆኑ እኛ ያልነው ካልሆነ በስተቀር በማለት ሲያላዝኑ የሚውሉ ውሾች ናቸው

በቀድሞዎቹ አፄዎችና ከዚያም ወዲህ ኢትዮጵያን በጉልበት ያስተዳደሩ አምባገነን መሪዎች ብዙዎችን ዘንግተው ኖረው አልፈዋል፤ከለውጡ ወዲህ አገራዊ ፓርቲ መመስረት የቻለው ብልፅግና ግን ሁሉን አካታች ሆኖ ታላቋን ኢትዮጵያ በብቃት እየመራ ነው፤በለውጡ የተመዘገቡ ድሎችን በተመለከተ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ከሰሞኑ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተጨባጩን እውነታ ይናገራሉ

“ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተረሱ ብሔር ብሔረሰቦች በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ መንግሥት እና ፖለቲካ ውስጥ በደንብ እየታዩ ነው። ቀድሞ ውሳኔ ሰጪነትም ላይ አቅም አልነበራቸውም። ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ትልቅ ለውጥ እየመጣ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክም በአግባቡ እየተገለፀ ነው። በእርግጥ አሁንም ችግሮች አሉ። ይህን አሁንም የማይቀበሉ እና ዴሞክራሲን የማይፈልጉ አሉ። የኢትዮጵያን መፍረስ የሚፈልጉም አሉ።እነዚህ አካላት ያልገነቧት ኢትዮጵያ አትጥማቸውም። ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ውስጥ እነርሱ ያላቀበሉት ብረት፤ ያልነኩት ፖለቲካ አይጥማቸውም። ሆኖም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ እየታተሩ ያሉት አሁን ነው ማለት ይቻላል።”


ምሁር ተብዬዎቹ በአማራ ሕዝብ ስም በመነገድ ላይ የሚገኙ ጽንፈኞች በተለያዩ የውጭ አገራት ተቀምጠው፤ከእነ ቤተሰባቸው የተደላደለ ኑሮ ላይ ሆነው በአገር ቤት የሚገኙ የደሃ ልጆችን በለው ቁረጠው ፍለጠው የሚል ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ አሁን የትም መድረስ የማይችሉ መሆናቸው ተረጋግጧል ነገር ግን ውስጥ ለውስጥ  የተለመደ ጩኸታቸውን ቀጥለዋል የቁራ ጩኸት ምን ያመጣል?

ለማንኛውም ከሰሞኑ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ብቻ የተለያዩ አስፀያፊ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል እነዚህ በአማራ ሕዝብ ስም የሚነገዱ ጽንፈኞችን እብጠትና ጥላቻ ለታሪክ አስቀምጠነዋል፤በማድረግ ላይ ያሉትን ሁሉ መዝግበን እየያዝን ነው፤ሊተገበሩ የማይችሉ ህልሞቻቸው እነዚህ መሆናቸውን ተረድተናል ወደ ልቦናቸው በደም ፍላት ደመ ነፍስ ያሉትን ተመልሰው ይመርምሩ!

''ወደ አባታችን ወደ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት እንገስግስ'',

''መንግሥትን ለማፍረስ ጊዜው አሁን ነው''

“ኢትዮጵያን መግዛት የሚችለው አማራ ብቻ ነው''

“አዲስ አበባ ሚኒሊክ ገንብቶ የሰጠን የአማራ ከተማ ናት

“ኦሮሞ ወደ መጣህበት ወደ ማዳጋስካር ግባ''

“ክልሎች ይፍረሱ ህገ መንግስቱ ይቀደድ''

“አማራ ወደ ቤተ መንግሥትህ ተመለስ''

“የሚኒሊክን ታሪክ እንደግማለን''

“መከላከያ ሰራዊቱ ሸኔ ነው''

“አራት ኪሎ ያለው ሸኔ ይውጣ”

“እኛ የሚኒሊክ ትውልዶች ነን”

“ቤተ መንግሥቱ የእኛ ነው''

“በምንጃር በኩል አራት ኪሎ ቅርብ ነው እንፍጠን''

“በሚሊዮኖች አልቀን አራት ኪሎን እንይዛለን'' የመሳሰሉ መፈክሮችና መልዕክቶች በሰሞኑ ኩነት ላይ በስፋት በጎዳና ላይ ነውጡ አስተጋብተዋል ይህን ሁሉ መፈክርና መልዕክት በእብሪት ያስተጋባው ሃይል አሁን የት ነው ያለው?እምጥ ይግባ ስምጥ አይታወቅም

ጽንፈኞችና የልዩ ሃይል ፍቅራቸው ህመም

“ጉድ አንድ ሰሞን ነው” እንዲሉ ጽንፈኞች ለልዩ ሃይል ታጣቂዎች ያላቸውን ከፍተኛ ፍቅር አይተናል፤በዚህ የአክራሪ ጽንፈኞች ፍቅር ምክንያት የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ጥቂት አባላት ወንድሞቻችን ተሳስተው ለጉዳት መጋለጣቸውን ተረድተናል

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሰሞኑ በልዩ ሃይል አደረጃጀት ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ እንዳረጋገጡት ፋኖ የሚባለው ሕገ ወጥ አደረጃጀት ከልዩ አባላት ላይ መሳሪያ ለመንጠቅ ሲል ጉዳት አድርሷል  በጣም ያሳዝናል! ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በጽንፈኞች አነሳሽነት እንደሆነ መገንዘብ ይገባል

አሁን ጩኸቱ አልፏል ስሜት ላይ የተመሰረተው ፍቅርም እየሟሸሸ ነው፤አብዛኞቹ ክልሎችም መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የልዩ ሃይል አደረጃጀት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፤የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት በክልሉ የልዩ ሃይል አደረጃጀት ስራ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፤በኦሮሚያም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል

የሚበዛው የአማራና የኦሮሚያ ክልል ነው ሁለቱም በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ለህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት አመልክተዋል፤ያጠናቀቁ ክልሎችም እንዳሉ ይታወቃል ስለዚህ ፕሮግራሙ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተከናውኗል መልካም ነው

በዚህ ድል ጽንፈኞች በዝረራ ተሸንፈዋል፤መሸነፋቸውን ላለማመን አሁን ወደ ዘለፋና ስድብ እንዲሁም የአመራሮችን ስም ለይተው በመጥቀስ ስም በማጥፋት ተግባር ላይ መሰማራታቸውን እየተመለከትን ነው እንግዲህ “ልፋ ያለው………”ብለን አልፈናቸው ሄደናል እነርሱ ቆሞ ቀሮች ስለሆኑ ከቆሞ ቀሮች ጋር ባሉበት ከመቆም ወደፊት መሄድ እንደሚሻል መረዳት የምንችል ዜጎች ነን 



መሳይ መኮንን

Post a Comment

0 Comments