በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎች ጎብኝቷል

 



በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የልዑክ ቡድኑ በጉብኝቱ ሰማያታ የእምነበረድ ፋብሪካ እና ሸባ የቆዳ ፋብሪካን ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ፋብሪካዎቹ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው በፋብሪካዎቹ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውም ነው የተገለጸው፡፡
የክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች በበኩላቸው ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው እሁድ ሰላምን ለማጽናት እና ለትግራይ ክልል ህዝብ ያላቸውን አጋርነት በተግባር ለማረጋገጥ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በክልሉ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ዛሬ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት፡፡
source:ENA

Post a Comment

0 Comments