ነውረኞች ጊዜ እየጠበቁ የሚፈጽሙት አስነዋሪ ድርጊት ሊቆም ይገባል!



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 19,2015(YMN) የአማራ አክራሪ ጽንፈኞች ከአራት ዓመታት በፊት በጀነራል አሳምነው ጽጌ አመራር ሰጪነት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ዶክተር አምባቸው መኮንን እና ሌሎች ጠንካራ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮችን በልተዋል

ከዚያም በኋላ በተለያዩ ወቅቶች በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎችን በመግደል የክልሉን ሕዝብ አመራር የማሳጣት ድርጊት ፈፅመዋል

አሁንም ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ላይ ተኩረት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የአምስት ሰዎችን ሕይወት ዛሬ ሚያዝያ 19, 2015 ዓ.ም በመሃል ሜዳ በበለጠ ሸጋው በሚመራ የሰሜን ሸዋ ፋኖ ማጥፋታቸው እየተነገረ ነው


ይህ የሽብር ድርጊት ነው! በዚህ አሳቃቂ ድርጊት የክልሉ መንግስት አመራሮችና በአጠቃላይም ሕዝቡ ስጋት ውስጥ በመግባት ኑሮው እንዲናጋ፤እንቅስቃሴው እንዲገደብ፤በመንግስቱ ላይ መተማመን እንዳይኖረው ታስቦና ታቅዶበት የተፈፀመ የአረመኔዎች ድርጊት ነው

"የፈሪ ዱላ አስር ነው" እንዲሉ ጽንፈኞች መንግስትን ለመገልበጥ ያስችለናል ያሉትን በርካታ ዱላ ሰንዝረው ሊሳካላቸው አልቻለም፤ ከሽፈዋል በአቶ ግርማ የሽጥላና ሌሎች ዜጎች ላይ ዛሬ የፈፀሙት አስነዋሪ ድርጊት ደግሞ ተስፋ የቆረጡ መሆናቸውንና በዚህ ድርጊታቸው ቁጣ ተቀስቅሶ ብጥብጥ እንዲኖር ይረዳን ይሆናል በሚል በደመ ነፍስ የፈፀሙት ድርጊት ነው ማለት ይቻላል

ቅጥረኞቹ ይህን ድርጊት የፈፀሙት ከውስጥና ከውጭ ግፊት እያደረጉ ባሉ ቡድኖች እገዛ አማካይነት እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል

ከሰሞኑ የአማራ ክልል ባለሃብቶች የባንክ አካውንት መታገዱ ይታወቃል፤የባለሃብቶቹ የባንክ አካውንት በሚመለከተው የመንግስት አካል የታገደው ያለ ምክንያት አይሆንም ባለሃበቶቹ መሰል ግድያዎችን ሰፖንሰር ሲያደርጉ የቆዩ ሊሆኑ ይችላሉ አሁን ለተፈፀመው ግድያም የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ መጠርጠር ተገቢ ይሆናል አጀንዳ ማስቀየሪያ ስልትም ሊሆን ይችላል

ገዳዮች ያለምንም ድጋፍ ድፍረት ሊያገኙ አይችሉም! አይዞ ባዮች ከውስጥና ከውጭ በሚያደርጉት ድጋፍ የሚያገኙትን ጥቅም ከግምት በማስገባት በጭካኔ ፈፅመውት ሊሆን ይችላል፤የደህንነቱ መዋቅር  እውነቱን በጊዜው ማውጣቱ የማይቀር ይሆናል!

እስከዚያው የክልሉ አመራሮችና መላው የአማራ ሕዝብ  በመተባበር የአማራን ክልል ሰላም መጠበቅና ጥብቅ ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ችግሩ እኔን እስካል ነካ ድረስ ብሎ መዘናጋት ወይም ችላ ማለት ተጨማሪ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል የክልሉ መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በመተባበር መስራት ተገቢና አስፈላጊ ነው

"ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል" እንዲሉ ጽንፈኞች ራሳቸው አቅደው ያስፈፀሙትን ድርጊት "አብይ አህመድ ነው ያስገደለው"እያሉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን በመርጫት ላይ ይገኛሉ፤ይህ የተለመደው ፕሮፓጋንዳቸው እነ ዶክተር አምባቸውና ባልደረቦቹ በአሳምነው ጽጌ በተገደሉበት ወቅትም የነበረ ነው፤ተመሳሳይ ቅጥፈታቸውን በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል

ምሽቱን በአቶ ግርማ የሽጥላ ግድያ ምክንያት የክልል መንግስታት አመራሮችና ሌሎች አካላት የሃዘን መግለጫዎቻቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ 

Post a Comment

0 Comments