ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ!

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 15,2015(YMN) ዛሬ ከዓት በኋላ በወዳጅነት አደባባይ የተካሄደውን የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዓት በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ሞክሪያለሁ
ከሶስት ሰዓት በላይ ቆይታ የነበረው ይህ ስነ ስርዓት በጣም ብዙ ኩነቶች ተከናውነውበታል፤ስነ ስርዓቱ ደማቅና ቀልብን የሚይዝ ነው፤ በቂ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ስለመሆኑ የተፈፀሙ ክንዋኔዎች ሁሉ ማሳያ ናቸው "ጦርነት ይብቃ ሰላምን እናፅና" በሚል መርዕ ቃል ዛሬ የተካሄደው የምስጋናና የዕውቅና መስጠት ስነ ስርዓት ላይ የሰሜኑ ጦርነት ቆሞ ሰላም እንዲፈጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰብ አመራሮችና ታዋቂ ሰዎች የተዘጋጀው የምስክር ወረቀትና የኢትዮጵያ ካርታ ቅርፅ ተሰጥቷል
የተሰማኝን ላጋራችሁ!ስሜቴ የተደበላለቀ ሆኖብኛል ያለፈውን በምናብ አስታውሻለሁ ያለፈውንና የሆነውን መዘንጋት የሚቻል አይመስለኝም
የቀጥታ ስርጭቱን እየተከታተልኩ የጦርነቱ ሂደት መጥቶ ድቅን ይልብኛል
በጦርነቱ ምክንያት የደረሰው ጉዳት ከመኖሪያቸው አካባቢ የተፈናቀሉ ዜጎች በሴቶችና ሕፃናት ላይ የደረሰው እንግልት፤የጠፋው የሰው ልጅ ሕይወትና የወደመው ንብረት ሲታወስ ምነው አሁን ያለው ሁኔታ ያኔ ቢፈጠር ኖሮ ያስብላል
አሁን የተፈጠረው ሰላማዊ ሁኔታ ዘላቂ እንዲሆን ጦርነት ይብቃ ሰላምን እናፅና ብለናል መልካም ነው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለዚህ እንዲሰሩ እንዲተጉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፕሮግራሙ ማጠናቀቂያ ላይ በሳሙት ንግግር አደራ ብለዋል፤አደራውን ሁሉም ይወጣል የሚል ተስፋ አለ
ሰላም የሚያስፈለገው ለሁሉም ነውና የኢትዮጵያ መንግስት ከሸኔ ጋር የሚካሄደው የሰላም ውይይትም ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ተበስሯል ይህ አስደሳች ነው፤ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ውይይቱ በታንዛኒያ እንደሚጀመር አብስሯልጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሰላም ውይይቱ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ይፋ ከማድረግ አልፈው ዝርዝር ሂደቱን ባይናገሩም ሰላማችን እንዲበዛ ኢትዮጵያችን እፎይ እንድትል እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፤ ኢትዮጵያችን ሰላምሽ ይብዛ!



Post a Comment

0 Comments