በትግራይ ክልል ይፋዊ የስልጣን ርክክብ ተከናወነ


ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 27,2015(YMN) ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና ጀነራል ፃድቃን ገብረተንሳይ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተሹመዋል

በጌታቸው ረዳ የሚመራው አዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ዛሬ መጋቢት 27/2015 በመቐለ ከተማ በተካሄደ ሥነ ስርዓት ላይ ይፋ አድርጓል።
በዚህም ካቢኔ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነው የተሶሙ ሲሆን፣ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ ደግሞ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ሹመቱ ይፋ ሲደረግም የክልሉን መንግሥት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ አስረክቧል።
አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ (ባይቶና) ፖለቲካ ፓርቲ የተውጣጡ አባላትን በማካተተት ነው። የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ኹለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል ማግኘቱ ተገልጿል።
ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ መሆናቸውም ተገልጿል።



Post a Comment

0 Comments