ፊንፊኔ #ግንቦት 21/2015 (YMN) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ አንዲት በቅሎ መውለዷ ተነግሯል፡፡
የበቅሎዋ ባለቤት አቶ ብርሃኑ ተምትሜ በ2014 በቅሎዋን እንደገዟት እና ለማጓጓዣ አገልግሎት ሲጠቀሙባት መቆየታቸውን ተናግረዋል።
የበቅሎዋ መውለድ ክስተት እንዳስገረማቸው አንስተው÷ ውርንጭላው አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
በባኮ ቲቤ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት የእንስሳት ሐኪም የሆኑት ዶክተር ለማ አያለ በቅሎ ሲወልድ አይተው እንደማያውቁ እና ክስተቱ እንግዳ እንደሆነባቸው ገልፀዋል፡፡
ባለሙያው በቅሎ አትወልድም የሚለው እሳቤ በሳይንስ እና በባህላዊ መንገድ የታመነበት ጉዳይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ከአንድ ሚሊየን በቅሎዎች አንዳቸው ሊወልዱ እንደሚችሉ መግለጻቸውን የወረዳው ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
0 Comments