የቡርቴ ኃላፊነት መልቀቅ ጥያቄና እሰጥ አገባው



ፊንፊኔ #Ethiopia ሰኔ 20/2015(YMN) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ትናንት ይፋ ባደረገችው መረጃ በጤና ችግር ምክንያት ረጅም የእረፍት ጊዜ እንደሚያስፈልጋት በመጥቀስ በፈቃድዋ ስራ የመልቀቅ ጥያቄዋን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ሰኔ 5 ማቅረቧንና እስከ ነሃሴ 1/2015 ዓ.ም ድረስ ቀሪ ስራዎቿንና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን እንደምታጠናቅቅ ተናግራለች

ይህቺ ጠንካራ ዜጋ የዜግነት ግዴታዋን ሳትሸራርፍ ተወጥታለች የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆና በተወካዮች ምክር ቤት ከተሾመች በኋላ ያከናወነቻቸውን ስራዎች ታሪክ መዝግቦ ይዞታል

ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተጨባጭ ስራዋና አገልግሎትዋ አመስገነዋታል፤ይገባታል!6ኛውን አገራዊ ምርጫና የተለያዩ ሕዝበ ውሳኔዎችን በብቃት መምራት ችላለች

ብርቱካን ሚደቅሳ ሳያማት አሞኛል የምትል ውሸታም እንዳልሆነች መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቃል፤ይረዳል

የስራ መልቀቅ ጥያቄዋ ከመንግስት ጫና ጋር የሚያያዝ እንደማይሆን ይታመናል፤ እርሷም ጫና ቢኖርባት ኖሮ እንደማትደብቅ ይታወቃል፤የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስብእና ይህን አይፈቅድም ቡርቴ ደፋር ናት! ጠንካራ ሴት! በኢህአዴግ ጊዜ እንኳ በተግባር ያሳየችው ጥንካሬ በሁሉም ዘንድ ይታወቃል

ይሁንና በቡርቴ ስልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ጽንፈኞች ለምን ጨፈሩ?ይሆናል ብለው ያመኑትና የባጥ የቆጡን የሚቀባጥሩበት ይህ ክስተት ጽንፈኞቹና አንዳንድ አክቲቪስት ነኝ ባይ ግለሰቦች በይሆናል ትንታኔ እንደሚሰጡበት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም

ብርቱካን ሚደቅሳ ጀግናዋ ጠንካራ ኢትዮጵያዊት ያቀረበችው ጥያቄ ሕጋዊና ተገቢ ነው!የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን መርምሮ የሚሰጠው ምላሽ ይጠበቃል፤ ብርቱካን ሚደቅሳ የገነባችው የዴሞክራሲ ተቋም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአስተማማኝ መሰረት ላይ ተቀምጧል በሌላ አመራር ስራውን አጠናከሮ ይቀጥላል!እውነታው ይኸው ነው ለብርቱዋ ብርቱካን ጤናዋ ተመልሶላት ረጅም እድሜን እመኝላታለሁ! 

Post a Comment

0 Comments