ፊንፊኔ #Ethiopia ሃምሌ 17/2015(YMN) አቶ ዮሐንስ ቧያለው የአማራ
ክልል ምክር ቤት አባል መሆኑን አላውቅም ነበር፤ይህ ሰውዬ የክልሉ ምክር ቤት አባል መሆኑን መረዳት የቻልኩት ከሰሞኑ በባህር ዳር
በተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በሰጠው አንድ አስተያየት ነው
አቶ ዮሐንስ ቧያለው በምክር
ቤቱ ጉባኤ ላይ ያቀረበው አስተያየትና ከዚያ በሁዋላ በወጣው ሚስጢራዊ መረጃ ሁለት ቦታ ቆሞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል፤መቼም
ቢሆን ይህን እውነት መካድ የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል
በትዕቢት የተወጠረ መሆኑን
በሚያሰማቸው ንግግሮች የሚገልፀው ይህ ግለሰብ በምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ ያነሳቸውን አንዳንድ ነጥቦች በማንሳት ማየት ጠቃሚ ይሆናል
ይህ ሰው ስለ ሸገር ከተማ
አስተዳደር ጉዳይ አንስቶ ተቃውሞውን አሰምቷል፤የሸገር ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ተቆርሶ ሲመሰረት የአማራ ክልል ለምን ዝም
ይላል?ሲልም የቁጭት ጥያቄውን አቅርቧል፤የሸገር ከተማ አስተዳደር ከቀድሞው በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞንና በምሁራን ጥናት
የውሳኔ ሃሳብ የቀረበባቸውን የፊንፊኔ አካባቢዎች በመያዝ የተመሰረተ መሆኑ በግልጽ ይታወቃል
ቆሞ ቀርነቱን በሚያሳይ መልኩ
የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ለምን መንገድ ይጠብቃል?ሲልም ጠይቋል፤አሁን ልዩ ሃይል የሚባል አደረጃጀት የሌለ መሆኑም ይታወቃል
ግለሰቡ አሁን ይፋ ያደረገው
አቋም በአማራ ክልል ምክር ቤት ውስጥ እያለ ከጽንፈኛ ሃይሎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል
ተጨባጩን እውነታ መካድ ካልተፈለገ
በስተቀር አቶ ዮሐንስ ቧያለው በምክር ቤቱ ውስጥ ሆኖ ለጠላት በግልጽ እየሰራ ነው፤ይህ ደግሞ በአደባባይ ላይ ይፋ ሆኗል ሚስጢራዊው
የስልክ ልውውጥ ከመውጣቱ በፊትም ይህ ደፋር ሰው በምክር ቤቱ ውስጥ ባሰማው ንግግር ከድንበር ያለፈ ደፋርነቱን ይፋ አድርጓል
በአማራ ሕዝብ ላይ የተደረገ
የሴራ ፖለቲካ አለ ብሎ የሚከራከረው ይህ ሰውዬ ልዩ ሃይል በፌዴራል መንግስት ሲፈርስ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዝም ማለት አልነበረበትም
ሲል ይከራከራል፤የልዩ ሃይሉ አደረጃጀት እንዳይቀየር የፈለገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግልጽ መሆኑ የሚታወቅ
ነው
የአማራ ክልል የፀጥታ ችግር
አለ እያለ፤ የመከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ውስጥ ምን ይሰራል?ሲልም ይጠይቃል፤የክልሉ መንግስት ፈቅዶ ነው መከላከያ የገባው?ብሎ
መጠየቁም ተሰምቷል
ይህ ተስፋ የቆረጠ ሰው
“በምክር ቤት ውስጥ እንዲህ የምናገረው ነገ ስለምገደል ነው”ብሎ ሲናገርም ተሰምቷል
ምክር ቤቱ በወሰነው መሰረት
በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር በቀጣይ የሚካሄደው ድርድርም ለጊዜ መግዥያ የሚያገለግል መሆኑን አቶ ዮሐንስ ቧያለው ኋላ
ላይ ይፋ አድርጓል
ከምክር ቤቱ ጉባኤ መጠናቀቅ
በሁዋላ በወጣው ሚስጢራዊ መረጃ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በውስጥና ወጭ ከሚገኙ ጽንፈኛ ሃይሎች ጋር ግልጽ ግንኙነት በማድረግ በመስራት
ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል
የክልል መንግስት ምክር ቤት
አባል ሆኖ ከጽንፈኛ ሃይሎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በማድረግ መስራት የሚቻለው በየትኛው የአሰራር ስርዓት መሰረት ነው?መቼም እንደ
የትኛውም የክልል ምክር ቤቶች የአማራ ክልል ምክር ቤትም የራሱ የአሰራርና የስነ ምግባር ደንብ ይኖረዋል
ታዲያ አቶ ዮሐንስ ቧያለውና መሰለቹ ግለሰቦች በምክር ቤቱ የአሰራር ስርዓትና የስነ ምግባር ደንብ መሰረት
የማይጠየቀው ለምንድነው? እንዲያውም ከዚህ ሰውዬ ላይ ያለመከሰስ መብቱ ተነስቶ በህግ መጠየቅ አለበት!መከላከያ በዚህ ሄደ፤በዚህ መጣ እያለ መረጃ መስጠቱም በአገር ክህደት ወንጀል ለያስጠይቀው የሚችል ነው
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ
የሃላፊነት ቦታዎች ሹመት ተሰጥቶት አሻፈረኝ ሲል የቆየው አቶ ዮሐንስ ቧያለው አሁን ላይ ሰርተን እንዳንበላ ተከልክለናል ሲልም
በለውጡ አመራር ላይ ቅሬታ እንዳለው ይፋ አድርጓል
አቶ ዮሐንስ ቧያለው በለውጡ
መጀመሪያ ወቅት ወደ አሜሪካ በመጓዝ በውጭ ለሚገኙ ጽንፈኛ የአማራ ኃይሎች “ከፊት ያለው አረፋ ነው ለእኛ ተውት” ብሎ ቃል በመግባት
ለውጡ እንዲቀለበስ እንደሚሰራ ያረጋገጠ መሆኑ ይታወቃል
የአማራ ጽንፈኞች በቅድሚያ
የአማራን ክልል መንግስት ከስልጣን እናወርዳለን ብለው በማለም የሰሩ መሆናቸውን ተግባራቸው አረጋግጧል፤ይሁን እንጂ አሁን ባለው
ተጨባጭ ሁኔታ አቶ ዮሐንስ ወገንተኝነቱን አሳይቶ የሰራላቸው የውስጥና የውጭ ጽንፈኛ ሃይሎች አቅም ኖሯቸው በአጠቃላይ ብልጽግና
መራሹን የኢትዮጵያ መንግስት ከስልጣን የሚያወርዱበት ሁኔታ የሌለ መሆኑ “ፀሐይ የሞቀው አገር ያወቀው” ጉዳይ ሆኗል
0 Comments