የአማራ ሕዝብ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉት ከውስጡ የወጡ ጽንፈኞች ሲወገዱ ብቻ ነው!




ፊንፊኔ #Ethiopia ሃምሌ 18/2015(YMN) በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ጥይት በመተኮስና ህዝብን እረፍት በመንሳት የአማራ ሕዝብ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም ጉዳዩ የሚመለከተው ሁሉ ልብ ሊል ይገባል!አስተኳሹ ላይም ትኩረት መደረግ አለበት!

የብልጽግና ፓርቲ ባለው ጠንካራ ሕገ ደንብ መሰረት አቶ ዮሐንስ ቧያለውና መሰል ሰርጎ ገቦች ላይ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል
ለዚህ ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ መዋቅር ከፍተኛ ኃላፊነትና ስልጣን አለው፤ብልጽግናን የመረጠው የአማራ ክልል ሕዝብም ጉዳዩን በጥሞና ተመልክቶ ለመረጠው ፓርቲ ድጋፍ ማድረግ ካልቻለ አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ነገር ከድጡ ወደ ማጡ መሆኑ የሚቀር አይመስልም
ወልድያና አካባቢው ላይ የተኩስ ልውውጥ ሳይሆን የተኩስ ድምፅ ነው የነበረው የሚል ማስተባበያ ለውጭ ሚዲያ መስጠት አሁን ምን ጥቅም አለው?
በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ በመፍጨርጨር ላይ ለሚገኙ ጽንፈኛ ኃይሎች ምቹ ሁኔታ በሚፈጥር መልኩ ስማችን አይጠቀስ እያሉ ለውጭ ሚዲያ መረጃ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሰዎችም የተሰጣቸውን የቤት ስራ በመወጣት ላይ የሚገኙ ይመስላል
ቀደም ሲል ወያኔ በለኮሰችው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ እንግልት ውስጥ የቆየው የአማራ ክልል ሕዝብ ከመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የክልሉ የፀጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ሰላምና ፀጥታውን ሊያስከብር ይገባል
አለበለዚያ በእነ ዮሐንስ ቧያለው ተላላኪ ተሽሎክላኪዎች ሰላሙን አጥቶ ከምርትና ዕድገት ስራውም ተስተጓጉሎ ሰላማዊ ሕይወትና ኑሮ ሊቀጥል አይችልም!
የአማራ ክልል ምሁራን፤የአገር ሽማግሌዎች፤ታዋቂ ሰዎችና ለአገሩ ማሰብ የሚችለው ዳያስፖራ ማህበረሰብ በክልሉ ውስጥ ለመፈንጨት ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ ጽንፈኛ ቡድኖችን እረፉ ሊሉ ይገባል "ሳይቃጠል በቅጠል" ይላል ያገሬ ሰው
ተወደደም ተጠላ የአማራ ሕዝብ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ሊያገኝ የሚችሉት ከውስጡ የወጡ ጽንፈኞች ሲወገዱ ብቻ ነው! በክልሉ ውስጥ ተልዕኮ ወስደው ተደብቀው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ጽንፈኞች በአስቸኳይ ካልተወገዱ የክልሉ ህዝብ ተጎጂ ይሆናል
ይህን እውነት በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል መንገድ ከተዘጋ፤የልማት ስራ ቀጣይነት ከሌለውና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ቀጣይነት የማይኖረው ከሆነ ከውጭ በሚደረግላቸው ድጋፍ ምክንያት ሞራል ያገኙ ጽንፈኞች እስከ አሁን ካደረሱት በላይ ጉዳት የሚያደርሱበት ሁኔታ ሊፈጠር ስለሚችል ከዘላቂ ችግር ጋር ከመዝለቅ ይልቅ ህብረተሰቡ በውስጡ የሚገኙ ጽንፈኞችን መንጥሮ ሊያወጣ ይገባል!

Post a Comment

0 Comments