የዲፕሎማሲያችን ድልና ስኬት ተጨባጭ ነው!

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ነሃሴ 14/2015(YMN) አትዮጵያችን በዲፕሎማሲው ዘርፍ ያስመዘገበችው ድል የሚታይና ተጨባጭ ነው፤የዲፕሎማሲው ድል የተመዘገበው የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የለውጡ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት በመቻላቸው ነው

ሁለት አመታትን በፈጀው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ዲፕሎማሲያችን እንዲሽመደመድ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፤በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብቻ ለመወያየት ከ12 ጊዜ በላይ እንዲሰበሰብና እንዲወያይ ሃያል ነኝ በምትለው አሜሪካ ጫና ተደርጓል

የመጣባትን መከራ በመቋቋም ልምድ ያካበተችው ኢትዮጵያችን በሁሉም የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ በጠንካራ ልጆችዋ ተጋድሎና በወዳጆቿ ድጋፍ የተከፈተባትን ዘመቻ መመከት ችላለች

አደጋው የከፋው ወያኔ በስልጣን ቆይታዋ ከአገር የዘረፈችውን ሃብትና ገንዘብ ተጠቅማ ወደ አጣችው ስልጣን ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በማድረጓ እንደሆነ ይታወቃል፤ይህ እውነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የሚኖር ይሆናል

በወቅቱ የመቀዝቀዝ አዝማሚያ አሳይቶ የነበረው የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጠንካራ እርምጃ ወያኔ በመሸነፏ ምክንያት ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ወዲህ በቅፅበት የተለወጠ ሆኗል፤በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስኬት ተጨባጭ መሆኑ እየታየ ነው፤የትኛውም ምክንያት ቢደረደር ይህን እውነት መካድ አይቻልም ኢትዮጵያ ደማቅ የዲፕሎማሲ ድሎችን ተጎናጽፋለች

ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ለጁንታው ከፍተኛ ድጋፍ ስታደርግ የቆየችው አገረ አሜሪካ አንዳንድ የጣለቻቸውን ገደቦች አንስታለች፤አሜሪካ ይህን ያደረገችው ጁንታው አቅመ ቢስ ሆኖ ባልተጠበቀችው ሁኔታ መሽመድመዱን በመረዳቷ እንጂ ለኢትዮጵያችን አስባ እንዳልሆነ እናውቃልን

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከአሜሪካ በተጨማሪ ሌሎች ወዳጅ አገራትም እንደተለመደው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት አጠናክረው ቀጥለዋል፤ይህ ወዳጅነት ከሴራ የፀዳና በጋራ ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሆኖ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ጽኑ ፍላጎት አላት

አገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በመከባበርና በጋራ ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑ ይታወቃል፤ትናንት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፊንፊኔ የገቡት የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንም በዚህ መሰረታዊ እውነት ላይ ተመስርተው ኢትዮጵያን የጎበኙ መሆኑ ግልፅ ነው

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ዐብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት “እያደገ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በመከባበር እና ለጋራ እድገት የጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ” መሆኑን አረጋግጠዋል፤ዘላቂ ልማትን ለማስቀጠል ትብብራችንን እንቀጥላለንም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያላቸው ጥላቻ እያቅበጥበጣቸው ያለውና ናላቸውን ያዞራቸው የጠላት ቅጥረኞች ጽንፈኝነታቸውን በመቀጠል በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጉብኝት ምክንያት መንጨርጨራቸውን ተመልክተናል

የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ንዴት፤ብግነትና ተስፋ መቁረጥን ያከናነባቸው ባንዳዎች በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች መካከል ሰባት ስምምነቶች መፈረማቸውን ሲሰሙ ደግሞ የተደረገውን ስምምነት ለማጣጣል ሞክረዋል

የኢትዮጵያ ድፕሎማሲ ስኬት በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ሊደበቅ ከማይችልበት ደረጃ አልፏል!ለጎረቤት አገራት ተገቢ ትኩረት ከመስጠት ጀምሮ ከሁሉም የዓለም አገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በተጨባጭ ድሎች ታጅቦ ተጨማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል!ይብላኝ ለጠላት ቅጥረኞች!

 

 

 

 

 

 

Post a Comment

0 Comments