"የምናብ ግድያና ድምሰሳቸውን እየሰማን፤ የድል ማማችን ላይ በከፍታ አለን"
የማህበራዊ ሚዲያ ምንደኞች ለከት የለሽ የፈጠራ ድርሰት በጣም አስቂኝ እየሆነ መጥቷል።
በእጁ የያዘው ብርጭቆ በድንገት ወድቆበት በሚፈጠረው ድምጽ "ልቡ የሚከዳው ድንጉጥ" ውሎበት ስለማያውቀው ጦርነት የሩቅ አዝማች ሆኖ በቃላት ናዳ ብዙ ሲናገር ይገርማል።
በማገዳደል፣ደም በማፋሰስና የህዝብን የሰቆቃ ዕንባ በማብዛት "ምኞቴ ይሳካልኛል" ባይ የስደት አውደልዳይ ከክረምቱ ዝናብ የበዛ የሀሰት ዶፍ ቢያዘንብ ያው "ምኞት አይከለከልም" ይሉት ሀገራዊ ብሂል አለና ከዚያ የሚያልፍ አይደለም።
እነዚህ "ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ" ይሉት አይነት ከንቱ ኳታኞችን እኩይ መሻት የወለደው ቅዠታዊ ሀሰትን ዕውን የሚያምን ካለ እጅግ በጣም ያሳዝናል።
ለነገሩ እኛ የምንሰራውን የምናውቅ፣ግብ ያለን፣እያንዳንዷ እንቅስቃሴያችን ከሀገርና ህዝብ ጥቅም ውልፊት እንዳይል አድርገን የምናስኬድ ነን።እናም በወሬ ናዳ ኪሱን ለማድለብ የሚጥር የሀሰት ነጋዴ ድርሰት ብዙም አያሳስበንም ሥራችን ሠላምን ማምጣት ነውና።
ይህን ጠንቅቀን ስለምናውቅም በግዳጅ አፈጻጸም ስምሪቶቻችን ሁሉ፤ባለማወቅ የተሸነገለን ወጣት እኩያኑ እንደቀመሩለት ለማገዶነት እንዳይዳረግ እና እውነቱ ተገልጦለት ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ሰፊ ዕድል በሚሰጥ አርቆ አሳቢነት ማስኬዳችን በብዙ አትርፎልናል።
ብዙዎች ከሸንጋዮች የጥፋት መንገድ ወጥተው ዛሬ ላይ ግንባር ቀደም የህዝብ ሰላም አስከባሪነት ሚናን መወጣት እንዲችሉ ማድረግ መቻላችን በእጅጉ ያስደስተናል።
በዚህ ጥበብ የተሞላበትና አስተውሎት በተላበሰ ስኬታማ ግዳጅን ጥርት አድርጎ መከወን የመቻላችን ሞያዊ ብቃት "የባህር ማዶ የሩቅ እብደት አዝማቾችን ደባ እርቃን ያስቀረ ሆኗል።"
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፤"የጨፍኑ ላሞኛችሁ ባይ የማህበራዊ ሚዲያ ሸቃጮች የሀሰት ልፈፋ አልቆመም።"
"የምናብ ግድያና ድምሰሳቸው ባዶ ጩኸት እየሰለለ የመጣም ቢሆን አልቆመም" ። "እኛ ግን ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሰላምን አድማስ እያሰፋን የድል ማማችን ላይ በከፍታ በኩራት ጸንተን አለን።"
እንደ ጀግኖች አትሌቶቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን እያኮራን ሰንደቃችንን በከፍታ ማውለብለባችን የማያቆም ተግባራችን ነውና።ይህ በድል የደመቀ ጉዟችን ይቀጥላል። #ENDF #Ethiopia #ETH
Source:ENDF fb
0 Comments