የአንዳንድ ኤርትራዊያን መንጨርጨር ምክንያቶች




ፊንፊኔ #Ethiopia ጥቅምት 20/2016(YMN) በዚህ ጽሑፍ የቀረቡ ሃሳቦችና ድምዳሜዎች ለኢትዮጵያ መልካም አመለካከት ያላቸውን ቅን ኤርትራዊያንን በሙሉ አይመለከቱም!

የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ፍላጎትን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ለተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የሰጡት ማብራሪያ በመገናኛ ብዙሃን በይፋ ከተሰራጨ በኋላ አንዳንድ ኤርትራዊያን በአደባባይ ወጥተው ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መግባታቸውን በግላጭ ነገረውን እኛም ታዝበናቸዋል፣አሁንም በትዝብት እየተመለከትናቸው ነው

ፍርሃታቸውን በውስጣቸው ይዘው ጭጭ ቢሉ ይሻላቸው ነበር፣ግን በውስጣቸው በቅሎ  ያደገው ሴራና ተንኮል አላስቻላቸውማ!በፍርሃታቸው ግፊት በሚመስል ሁኔታ አሁንም አፈ ቀላጤዎቻቸው በሚዲያ ላይ ፊት ለፊት ወጥተው አንዳንድ ታዋቂ የኢትዮጵያ ሰዎችንና  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን መዝለፍ ጀምረዋል

እንግዲህ  ስድብና ዘለፋ የትንሽነት ምልክት ነውና ያው ትንሽ ስለሆኑ ትንሽ መሆናቸውን የማናውቅ ይመስል ትንሽነታቸውን ደጋግመው ሲነግሩን ሰንብተዋል

አክቲሺስት ስዩም ተሾመና ዩቱበር ደሳለኝ አበራን በአካል ቢየገኟቸው ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ መናገር  ለአዕምሮ ከባድ ይሆናል፤ምክንያቱ እውነት ተናግረው ተንጨርጫሪዎቹን ማጋለጣቸው ነው

የመንጨርጨራቸው ምክንያት ብዙ ቢሆንም ከብዙ በጥቂቱ ማንሳት አስፈላጊ ነው፣እነርሱ ለከት እጥተው እንዳሻቸው ሲናገሩ እኛ እንደ ኢትዮጵያዊያን በጨዋነት ዝም የምንልበት ሁኔታ የለም!መኖርም የለበትም! ወደ መንጨርጨራቸው ምክንያት ስመለስ:

የመጀመሪያው የመንጨርጨራቸው ምክንያት ትንሽ መሆናቸው ነው፣ትንሽ ስለሆኑ በጣም ይፈራሉ፣ታላቋን  ኢትዮጵያ በጣም ይፈሯታል ከተነሳች ትውጠናለች ብለው ይሰጋሉ፣ምን ያንቦቀቡቃቸዋል?እኛ እንደ አገር ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተለየች አንድ ሉአላዊት አገር መሆኗን አምነን ከተቀበልን ሰነባብተናል፣እንዲያውም ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፤ለማንኛውም ትንሽነታቸው የበታችነት ስሜት ውስጥ ከቷቸው በጣም መቸገራቸውን ተገንዝበናል


በእርግጥ ጥንት በኤርትራ ፍቅር የተነደፉ አንዳንድ ሃይሎች አሁንም የኤርትራ ጉዳይ ነሸጥ እንደሚያደርጋቸው ይታወቃል፣እንደ አገር ግን ኢትዮጵያ የኤርትራን      ጎረቤት አገርነት መቀበሏ ዓለም ያወቀው ፀሃይ የሞቀው ጉዳይ ነው

ሁለተኛው የመንጨርጨራቸው ምክንያት ቅናትና ምቀኝነት ነው የኤርትራ ሰዎች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት አይሹም፣ለዘመናት ቆይቶባቸው ያሽመደመዳቸው የዓለም አቀፍ ህብረተሰብና የአሜሪካ ማዕቀብ ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ አድርጓቸዋል

በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ የባህር በር አግኝታ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ያስፈራቸዋል፣ፍርሃቱ  ደግሞ ሳይወዱ በግድ  በቅናትና ምቀኝነት እንዲንጨረጨሩ ያደርጋቸዋል

ተንኮሉ ወዲ አፎም አርፎ እንዳይቀመጥ የወጣትነት ባህሪው በእርጅና ዘመንም የለቀቀው አይመስልም፤ኢሳያስ የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት ይፋ በተደረገበት ማግስት ልዑካኖቹን የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ወደሆነችው ግብጽ ለምን ላከ? ብለን እንጠይቅ!ይህ ውሳኔ የለመዱት ሴራ ውጤት መሆኑን መገንዘብ ይገባል!የኤርትራ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በባህር በር ጉዳይ ላይ ከሰጡት ማብራሪያ በኋላ ወዲያውኑ የደስታ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ያዞረ መሆኑ ተረጋግጧል

ህግደፍ ሻዕቢያ ከውጭ ጠላት ጋር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ቦርቧራ ጋርም ግንኙነት እንደፈጠረ የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፤ይህን ስናውቅ ጃውሳ ያለምክንያት እንዳላቅራራ እንረዳለን

ግን ደግሞ ሁሉም ከተካኑበት ሴራና ተንኮል ውጭ አቅመ ቢስ ልፍስፍስ ስለሆኑ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ይታወቃል፤መፍጨርጨራቸው ስለማይቀር ኤርትራዊያን ወገኖችን ይዘው እንዳይጠፉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል

እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኢትዮጵያ ውስጥ 300 ሺህ ኤርትራዊያን በመኖር ላይ ይገኛሉ፤የሻዕቢያ ሴራ በእነዚህ የኤርትራ ዜጎች ላይም እንቅፋት እንደሚሆን ግልፅ ነው፤በባህሪያቸው ተፅዕኖ ምክንያት አርፈው ይቀመጣሉ ተብሎ አይታሰብም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ዜጎቻቸው ከመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም፤ይህ መሆኑ ሲረጋገጥ ደግሞ ታሪክ ሊደገም ይችላል!

አዋጩ ነገር ሰላም!መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ልማት ነው ከዚህ ውጭ ሌላው የተለመደው የጦርነት አማራጭ ፍፃሜን ሊያመጣ ይችላል፤ለኤርትራ ሕዝብ የሚያስብ አመራር ካለ ምርጫውን የጥፋት ሳይሆን የመልካም ግንኙነትና የጋራ ልማትና ዕድገት ያደርጋል!

 

Post a Comment

0 Comments