ፊንፊኔ #Ethiopia ሕዳር 04/2016(YMN) የውስጥና የውጭ ጠላት ተቀናጅቶ ዋና ትኩረቱ ምን ላይ እንደሆነ ከሰሞኑ ባወጣው ሰነድ ይፋ አድርጎልናል፤መልካም ነው ጠላት በቅንጅቱ አዲስ አጀንዳ አላመጣም ቀደም ሲልም በተደጋጋሚ ሞክሮ የከሸፈበት እንደሆነ እናውቃለን፤ቢሆንም “መረጃ አይናቅም አይደነቅም” ነውና በአዲስ መልክ መጥቷል የተባለውን የጠላት አጀንዳ በቅደም ተከተል ማየትና
መመርመር ጠቃሚ ነው
እነዚህ ጉዳዮች አዲስ ባይሆኑም ጠላት አጠናክሮ ሊቀጥልበት የመረጠው ስለሆነ አካሄዱን በማወቅና በመረዳት መከላከል በመጨረሻም ሙሉ በሙሉ
ድራሹን ማጥፋት ያስፈልጋል አጀንዳዎቹ በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው፤
§ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ማድረግ
§ የመከላከያ ሰራዊትን
በቀጣይነት ስም ማጥፋትና በሂደት ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ
§ የሐይማኖት ግጭቶች እንዲፈጠሩ በቀጣይነት መስራት
ናቸው፤በዝርዝር ስናያቸው
1ኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ
አህመድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ማድረግ፤
የሰላም ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት
እንዳያገኙ ቀደም ሲልም ስፍር ቁጥር የሌለው ሴራ ተግባራዊ ሆኗል፤በለውጡ መጀመሪያ ወቅት ላይ የመጡ በሚሊየን የሚቆጠሩ የጠቅላይ
ሚኒስትሩ ደጋፊዎች አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉም ተገልብጠው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ሆነዋል ተብሎ ቢለፈፍም ያለው ሁኔታ በተቃራኒው
ነው ሁሉም ተቃዋሚያቸው እንዳልሆነ ተረጋግጧል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በኃይል ከስልጣን እንዲወርዱ ከወዲያ
ወዲህ ተጠራርተው ተቀናጅተው በመፍጨርጨር ላይ የሚገኙ ምጢጢ ግለሰቦችና ቡድኖች ልክ እንደ እነርሱ ሌላውም ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምርሮ
የሚጠላና ከስልጣንም በኃይል እንዲወርዱላቸው የሚፈልግ ይመስላቸዋል፤ሁሉም የሚያስበው እንደ እኔ ነው ብለህ ስታስብ እንስሳነትህ
በአደባባይ ላይ ይታያል፤እየሆነ ያለውም ይኸው ነው
አሁን ባለው ሁኔታ ከብልጽግና የሚሻል አገርን መምራት
የሚችል ፓርቲ እንደሌለ አብጠርጥሮ የሚያውቀው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የብልጽግ ፓርቲና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋፊ ነው፤ይህን
እውነት ለማረጋገጥ ጊዜ የሚፈጅ ጥናት ማድረግ አያስፈልግም ወያኔ ሲያቀብጣት ጦርነት የጀመረችበትን ወቅት ብቻ ማስታወስ በቂ ይሆናል፤ከዚያ
በኋላ በተስፈኞች የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ከግብቻው ሳይደርሱ ተጨናግፈው ከመንገድ የቀሩት ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በመኖሩ ምክንያት
ነው
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስም በማጥፋትና ተቆጥሮ የሚታወቅ
በመአራራቸው የተመዘገበውን ውጤት በማጣጣል እንዲሁም የወጡበትን ብሔር
ለማሸማቀቅ በመሞከር የሚገኝ አንድም ፖለቲካዊ ትርፍና ስኬት እንደሌለ ተረጋግጧል፤ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን
በመስደብ፤ስማቸውን በማጠልሸት፤እንዲሁም የሚታይ ስራቸውን በመደበቅና በማንቋሸሽ የሚገኝ ትርፍ የለምና ጠላት ሆይ ተስፋህን ቁረጥ!
2ኛ የመከላከያ ሰራዊትን ስም ማጥፋትና
መገዳደር
ቀደም ሲል መከላከያ ሰራዊታችን በወያኔ ሴራ ምክንያት እንዲፈርስና እንዲሽመደመድ ቢደረግም
መከላከያ ከመፍረስ ተርፎ የአገር አለኝታና መከታ መሆን እንዲችል አስደማሚ በሆነ ሁኔታ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ተመልሶ ተገንብቷል፤እንዲያውም
የተዘጋጀው ለውስጥ ጠላት ሳይሆን ከውጭ ለሚመጣው ጠላት ነው ተብሎ ስንት ጊዜ ሲነገርህ ይሆን የሚገባህ?
የመከላከያ ሰራዊትን ስም በማጥፋትና ኃይሉን በመበተን
ለመገዳደር የሚደረግ የውስጥ ሴራ ምንም ውጤት ሊያስገኝ እንደማይችል ቀደም ሲል የተደረጉ ሙከራዎች አሳይተዋል፤መከላከያን ስትሰድብና
ስም ስታጠፋ የሚከተልህ እርምጃ ምን እንደሆነም በተግባር ያየኸው ስለሆነ ይህን መልሶ ለአንተ ለጠላት ተላላኪው መንገርና ማስረዳት
ለቀባሪው እንደማርዳት ይሆናል
ስለዚህ መከላከያን ለማዳከም በየትኛውም ስልት የሚደረግ
ሙከራ ዋጋ የሚያስከፍልህ መሆኑን ቅጣቱን ራስህ ቀምሰህ አጣጥመህ በተግባር አይተኸዋልና ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ አይሆንም
የኢትዮጵያ ህዝብ ከራሱ የወጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን
እንዴት እንደሚደግፍ መረጃ እንደሚሰጥ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግላቸው በተግባር ያሳየና አሁንም የተለመደ ድጋፉን በማድረግ
ላይ ይገኛል፤ባይሆንማ ኖሮ መከላከያ በገባህበት ገብቶ የሚገባህን ቅጣት ለመስጠት ይቸገር ነበር፤እንደለፈፍከውም በአራት ቀናት ውስጥ
አራት ኪሎ መግባት ትችል ነበር፤መላው ህዝብ አገሩ እንድትፈርስበት አይሻምና ከአብራኩ ለወጣው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ
ድጋፉን እያበረከተ ነው
ስለሆነም የመከላከያን ስም በማጥፋትና አድፍጦ ጉዳት በማድረስ
የሚፈርስ የመከላከያ ሰራዊት የለም፤የውስጡ ጠላት ተላላኪውና ዋናው ከውጭ ያለው ጠላት ተስፋቸውን ቢቆርጡ ይሻላቸዋል
3ኛ የሐይማኖት ግጭት እንዲፈጠር በቀጣይነት መስራት
ይህ አጀንዳም አዲስ አጀንዳ አይደለም፤ለተደጋጋሚ ጊዜ ተሞክሮ ጠላት የሚፈልገውን ውጤት ሊያገኝ ያልቻለበት
ነው፤ቀደም ባሉ ዓመታት ቤተክርስቲያናትና መስጊዶች ተቃጥለው እንዲወድሙ ተደርጓል
የሁለቱም ሐይማኖቶች ተከታዮች በቃጠሎ የወደሙትን ቤተ እምነቶች በመተባበር መልሰው ገነቡ እንጂ ጠላት
በሚፈልገው ሁኔታ ወደ ግጭትና መተላለቅ ገብተው እልቂት አልተፈጠረም፤የአጀንዳው ባለቤቶች እነ ማን እንደሆኑ ህብረተሰቡ ጠንቅቆ
ስለሚያውቅ ሃይማኖቶችን ተገን በማድረግ ስልጣን የጠማቸው ቡድኖች በሚሎኩሱት እሳት ለመቃጠል ፈቃደኛ አይደለም
የህብረተሰቡ ጽኑ ፍላጎት ሰላም፤ልማት፤አንድነትና ተከባብሮ በፍቅር መኖር እንደሆነ ይታወቃል፤ህብረተሰቡ
እኔን ካልደገፍክ እኔ እንደማስበው ካላሰብከ ለሚል የጠላት ተላላኪ ተገዥ እንዳልሆነ በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የታየው
ኩነት ተጨባጭ ምስክር ነው፤ክርስትያኑን እና እስላሙን እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮችን በማጋጨት ጠላት ተቀምጠህ የምትሞቀው እሳት
የለም
እነዚህ አጀንዳዎች እንደከዚህ በፊቱ መክሸፍ የሚችሉት በመላው ሕዝብ ተሳትፎና
እቢተኝነት ነው የሰላሙ ባለቤት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው የአፍራሾችን ሴራ
የማክሸፍ የሚቻለው በተለመደው ሁኔታ በመንቀሳቀስ ስለሆነ ሁሉም ለማንም ሳይሆን ለራሱ ሲል ይተባበር!
0 Comments