በፀረ ሌብነት ወር ስለ ሌቦች እናውሳ!



ፊንፊኔ #Ethiopia ሕዳር 06/2016(YMN) በሕዳር ወር ለሌቦች ጉዳይ ትኩረት ይሰጣል፤ስለ ሌቦች ይነገራል ሌብነት በሚቀንሰበት ስልት ላይ ጠቃሚ ውይይት ይካሄዳል፤ በአጠቃላይ ስለ ሌብነትና ሞሽላቃ ሌቦች በስፋት ይነገራል

የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትናንት በ20ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን አከባበር ላይ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፤የኮሚሽኑን መግለጫ ስሰማ  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በሌቦች ጉዳይ ላይ ከትናንት በስቲያ ከተወካዮች ምክር ቤት አንድ አባል ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ታወሰኝ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት ምላሽ የሌቦች ጉልበት ፈርጠም ማለቱን ያመለክታል፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “ስንቱ ይታሰራል” ነበር ያሉት?

ምላሻቸው ሌቦች መብዛታቸውንና አገር በሌቦች የሌብነት ድርጊት በአደጋ ላይ የምትገኝ መሆኗን ያመለክታል፤ምላሻቸው የማንቂያ ደውል ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል!

በስግብግብ ሌቦች አገራችን እንድትፈርስብን አንሻም አይደል? ጎበዝ በሌቦች ጉዳይ ላይ ነቃ እንበል! አገራችን የምትፈርስበት ሁኔታ ከተፈጠረ ሌቦች የሰረቁትን፤ህግን ከለላ በማድረግ የዘረፉትን የህዝብና የመንግስት ገንዘብ የት ተቀምጠው ይበሉታል?ማንስ ያስበላቸዋል?

እውነት ነው ሌቦች ባገኙት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ያግበሰበሱትን በሰላም ተቀምጠው የሚበሉበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፤ሌቦች ስለዚህ ጉዳይ ያስቡ ይሆን? ለነገሩ ህሊና ቢስ ስለሆኑ ስለዚህ ጉዳይ ማሰብ የማይችሉ ከንቱ ፍጡሮች መሆናቸው ይታወቃል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በአንድ ወቅት”ሌባ ቤት እንጂ አገር የለውም” ሲሉ ተናግረው ነበር እውነት ነው ሌባ የዘረፈውን የአገርና የህዝብ ገንዘብ ተጠቅሞ የራሱን መኖሪያ ቤት ሊገነባ ይችላል በዚህ የአይናውጣነት ድርጊቱም ቤት ሊኖረው ይችላል አገር ግን የለውም፤አገሩን ዘርፎ እንዴት አገር ሊኖረው ይችላል?ሞሽላቃ ሌባ! ህሊናህ እረፍት የለውም!

Post a Comment

0 Comments