ቀጥተኛነት የወታደር ጠባይ ነው አይደል?




ፊንፊኔ ታህሳስ 07/2016(YMN) የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሰሞኑን በሰጡት ማራቶን ቃለምልልስ በቀጥታ መሬት ያሉትን እውነታዎች ያለምንም ማሽሞንሞን ተናግረዋል።የኢትዮጵያ አየር ሃይል ቀንን በማስመልከት፣ እግረ መንገዳቸውን ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ከሰሞኑ ለሚዲያዎች የሰጡትን ማብራሪያ ተከትሎ እውነታው ያመማቸው፣ ሽንፈት ያሰከማቸው አካላት እንደተለመደው በዜጎች መፈናቀል፣ ግጭት፣ ሁከትና ብጥብጥ፣ የጥላቻና የጽንፈኝነት መርዝ እየረጩ ኪሳቸውን ማደለብ የለመዱ ማህበራዊ አንቂ ነን ባዮችና ዩቱበሮች አቃቂር ለማውጣት ቢሞክሩም ምንም ማግኘት አልቻሉም።ወታደር ቀጥተኛ ነው። ያለምንም ማሽሞንሞን ማቅረቡ ህመም ፈጥሮባቸዋል።

ፊልድ ማርሻሉ ከጋዜጠኞቹ ለቀረበለቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ጥምጥም ሳይሄዱ አካፋን አካፋ፣ ዶማን ዶማ ብለው መልሰዋል።የወቅቱን የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ፣ የሠራዊቱ አሁናዊ ቁመናና በጠላት እየተከፈተበት ያለው የስም መጥፋት ዘመቻ መንስኤ፣ እንዲሁም መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የወሰዳቸውንና እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች በመረጃና መሬት ላይ ያለውን እውነት መሰረት በማድረግ ብቁ ምላሽ ሰጥቷል።ከተሰጠው መረጃ የደም ነገዴዎቹ ይሄ ነው የሚባል ጉድለት አላገኙም።ምንም አለማግኘታቸው ደግሞ ከፊልድ ማርሻሉ ተሻግረው ጋዜጠኞችን ለመተቸት ሞክረዋል።

ነገሩ አልተገናኝቶ እና የጨነቀ ለት አይነት ነው።መሬት ላይ ጽንፈኞች የሚሠሩት ሥራ ውጤት አልባ ሆኖባቸዋል።ይህ ትልቅ ህመም ፈጥሮባቸዋል።ፊልድ ማርሻሉ ደግሞ በሚዲያ እውነቱን በቀጥታ ለሕዝብ መናገራቸው ሊመቻቸው አልቻለም።

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ ጩኸትና ጋጋታ ሁሉ መሬት ላይ ያለ ይመስላቸዋል።ሀሳብ አልቦ ስለሆኑ በሀሳብ መሞገት አልቻሉም።ማጭበርበሪያ መንገዱን የዘጋ ቃለ መጠይቅ ስለነበር ትርፍ ያስገኝልናል በሚል እና የሥራ ባህሪያቸው የሆነውን ግለሰባዊ ስብዕናን በሚነኩና ጥላቻን፣ መለያየትንና አንዱን ማህበረሰብ በማረከስ፣ሌላውን ደግሞ ተጠቂ በሚያስመስሉ ጉዳዮች ላይ ተጥደው ሰንብተዋል።ወሬ የሚያሞቁ እና ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው፣ ከእውቀትም ሆነ ከልምድም የራቁ ግለሰቦችን ያቀርቡና ከኢኮኖሚ፣ ከወታደራዊ፣ ከፖለቲካ አኳያ ትንታኔ እንደሰጡ በመደስኮር በየቀኑ ስርዓቱ እንዳበቃለት፣ መከላከያው እንደፈረሰ፣ የብልጽግና አመራሮች እንደተከፋፈሉ ወዘተ ይነዛዘሉ።

ይህ ሁሉ የዘወትር ዲስኩር በታቀደ መንገድ የመሪዎችን፣ የታዋቂ ግለሶቦችን፣ ማህበረሰቦችን ብሎም የሀገርን ገጽታና መልካም ስም ካላጎደፉ እኩይ ዓላማቸው ስለማይሳካ ነውር ብሎ ነገር ከእነርሱ አይጠበቅም።የሆነ ማህበረሰብ ጠበቃም ሆነው ይቀርባሉ።ጉዳዮ የፓለቲካ ገበያ አይደል? ዋናው ጉዳይ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚቀይረውም ሆነ የሚዘውሩት ሥራው ላይ ያሉ፣ ሀገራቸውን በመስዋዕትነት ወደ ብልፅግና ለማምራት ሌት ተቀን የሚሠሩ ጀግኖች መሆናቸው ነው።

ይህን እውነታ ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።ባንዳዎቹና በሰው ልጅ ደም ጥቅማቸውን ማካበት የለመዱት ማንነት ለፖለቲካ ገበያ የሚያቀርቡ ሸቀጮች ናቸው። ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት እና አላካኪነት ደግሞ ስልታቸው ነው።ዓላማችን ኢትዮጵያን ብልጽግና ማማ ላይ ማድረስ ነው።መንገዳችን መደመር ነው!

@L.Tulu

 

 

 

 

Post a Comment

0 Comments