በሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ የተጣበቁ ክሹፎች




ፊንፊኔ ጥር 11/2016(YMN) የፖለቲካ ፕሮግራም አዘጋጅተው በፖለቲካ ገበያ ውስጥ ራሳቸውን ለሕዝብ መሸጥ ያልቻሉ የከሸፉ ቡድኖች ከሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ መላቀቅ አልቻሉም፤ተስፋም አልቆረጡም፤ለዚህ ነው  የሚመላለሱበት!ተጣብቀውበታል

በሕገ መንግስቱ እውቅና ያለውን ሰንደቅ ዓላማ ሽረው በልሙጡ ሰንደቅ ዓላማ ፍቅር አቅላቸውን ያጡ ክሹፎች በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት እውቅና ያለው ሰንደቅ ዓላማ በመላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሙሉ ተቀባይነትና ድጋፍ ያለው መሆኑን ያውቃሉ

በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ላይ ያላቸው ጽንፍ ጥላቻና ንቀት ሕጋዊውን ሰንደቅ ዓላማ ሲመለከቱት ንቀትና ጥላቻቸው እንዲጨምር ብግነታቸውም ስር እንዲሰድ ያደርጋል

በዚህ ምከንያት በዘንድሮ የጥምቀት በዓል የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካቸውን በማፋፋም በተለያዩ ወቅቶች ሞክረው ያልተሳካላቸውን ጠብቀው ያላገኙትን ተመኝተው ያጡትን የመንግስት ግልበጣ ለማሳካትና ለዚህም መንደርደሪያ ለማድረግ አቅደው ተንቀሳቀሱ

ዕቅዳቸውን ተግባራዊ በማድረግ ዓላማቸው ግቡን እንዲመታ ለማድረግም ተላላኪዎቻቸውን መልምለው አሰማሩ፤ከመሃል አርማ የሌለው ”ልሙጥ” የተባለውን ባንዲራም አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እንዲሰቅሉ አደረጉ፤ለፈለጉት ግጭት ቅስቀሳ መነሻ ስልት መሆኑ ነው

ሁኔታው የገባው አገሩን የሚወደው የኢትዮጵያ ሕዝብ አልተቀበላቸውም መንግስትም የባንዳዎችን ፍላጎትና አካሄድ ስለተረዳ ነገሩን በጥበብ ያዘው፤ የትኛውንም ሙከራ ቢያደርጉም እንደማይሳካለቸው ዛሬም ተረጋገጠ ህብረተሰቡ በአንድነት ለሰላም በመቆም፤ለፀጥታ ሃይሎች ሙሉ ድጋፍ አደረገ  ጽንፈኞች ዘወር በሉልኝ አለ ግልፅ መልዕክቱን አስተላለፈ

የከሰሩ ጽንፈኞች በዘንድሮው የጥምቀት በዓል በለመዱት ሁኔታ ልሙጡ ባንዲራ በተላላኪዎች እንዲውለበለብ አድርገዋል፤ፊንፊኔ ላይም እንዲሁ ግጭት ለመቀስቀስ ተፍጨርጭረዋል የሰው ልጅ ደም እንዲፈስም ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው፤ይህማ ቢገኝ ኖሮ ደስታቸው እጥፍ ድርብ ይሆን ነበር ሊሳካላቸው አልቻለም፤ክሽፈታቸውን መከናነብ ግድ ሆኖባቸዋል

እንግዲህ “የአባ ግንባሩን በለው”ልጆች አልተሳካላቸውም ለማቀጣጠል የፈለጉት እሳት ሊቀጣጠልላቸው አልቻለም ከስረዋል፤ተላላኪዎቻቸው የተመነዘረላቸው ዶላር ምን ያህል እንደሆነ ራሳቸው ያውቁታል፤የዛሬ ክስረታቸውን ለማካካስ ምናልባት በቀጣዩ የአድዋ ድል በዓል ላይ መሞከራቸው አይቀርም! ለዚያ እዳው ገብስ ነው ልሙጡን ባንዲራ መያዝ የሰላማዊ ትግል አንዱ ስልታችን ነው ብለው ይመጡ ይሆናል

ለማንኛውም የሰንደቅ ዓላማው ጉዳይ በአገራዊ ምክከሩ ዘላቂ መፍትሔ ማግኘቱ የማይቀር ነው፤ሁሉም እስከዚያው ድረስ ይታገስ! እስከ አሁንስ ቆይተን የለ! የምን መጣደፍ ነው? በምክከሩ ቁርጡ ይታወቃል

ጥምቀት በዓላችን በሰላም ተከብሯል ኮሽ ያለ የለም! ግብረ ኃይሉም ባወጣው መግለጫ ይህን አረጋግጦልናል

የጥምቀት በዓል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገራችን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል።

የሃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች እና የበዓሉ ታዳሚዎች በየደረጃው ከሚገኙት የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በመሥራታቸው በዓሉ በድምቀት መከበሩም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የጋራ ግብረ-ኃይሉ ባዘጋጀው የፀጥታ ዕቅድ እየተመራ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት በማስቀደም ከዋዜማ ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘጥበቃና እጀባ ተግባራትን በማከናወን በዓሉ እንዲከበር ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችና አባላትን አመስግኗል፡፡

የሃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ ምዕመናን እና የበዓሉ ታዳሚዎች በዓሉ በድምቀት እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ላደረጉት ትብብርና ድጋፍም ምስጋና አቅርቧል።

በነገው ዕለት የሚከበረው የቃና ዘገሊላ በዓል እንደዛሬው ሁሉ በድምቀት እንዲጠናቀቅ ሕብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ኅብረተሰቡ እስከአሁን ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና ማቅረቡንም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመልክቷል፡፡

 

 

Post a Comment

0 Comments