በሕጋዊ ፓርቲ ስም ሕገ ወጥ መሆን ሊከለከል ይገባል!

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 04,2015(YMN) "አብን" የተባለው ፓርቲ የባልዲራስ እጣ ፈንታ የማይቀርለት መሆኑን በተግባር እያሳየ ነው፤ከሰሞኑ በልዩ ኃይል አደረጃጀት ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያስተላለፈውን ጠቃሚ ውሳኔ በመቃወም ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ያወጣው አብን ሁለት ቦታ መቆሙን እያረጋገጠልን ነው

የሰላማዊ ትግል ስም በመጠቀም ከምርጫ ቦርድ ዕውቅና ከወሰደ በኋላ መንግስትን በኃይል ለመቀየር ከሚሹ የውስጥና የውጭ ጽንፈኛ ቡድኖች ጋር በመወዳጀት አራት ኪሎ የመግባት ዕቅድ እንዲሳካ ዋና ተዋናይ መሆን ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል ቀጣይ ሊሆን አይችልም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይህን ጉዳይ አጽንኦት በመስጠት ሊመለከተው ይገባል! ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ፓርቲ በህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍና የተሟላ ግንዛቤ የሌላቸውን ወጣቶች በደመ ነፍስ በማነሳሳት ሁከት መቀስቀስ የሚችልበት ሁኔታ በተግባር እየታየ ህዝብ ላይ ጉዳት እየደረሰ በዝምታ መታለፍ ያለበት አይመስለኝም
እንደ ተቋም በሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እሳተፋለሁ ብሎ ባገኘው ምቹ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም በአቋራጭ ስልጣን ለመንጠቅ መንቀሳቀስ ሊኮነን ይገባል፤እንደዚህ ዓይነት አካሄድ የሚከተል የትኛውም አካል በህግ ተጠይቆ ወደ ህጋዊ አካሄድ መመለስ ይጠበቅበታል ለማንኛውም እኔ እንዲህ ብያለሁ

ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያጋኝም
የአብን ሁኔታ እኔ አላማረኝም

Post a Comment

0 Comments