ተፈላጊዎች በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መተባበር ተገቢ ነው!



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 23/2015(YMN) እነዚህ በሽብር ወንጀል የሚፈለጉ ናቸው፤የሚገኙት በውስጥም በውጭም እንደሆነ ይታወቃል በሕግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መተባበር አስፈላጊ ነው ጥቅሙ የጋራ ነውና
እነዚህ ተፈላጊዎች ለጊዜው ባይያዙም ጊዜው ሲደርስ ተይዘው ለሕግ መቅረባቸው የማይቀር ነው
መንግስት ከአነዚህ ጋርም ይወያይ!፤ከእነ እከሌ ጋርም ተዋያይቶ የለ እንዴ? ብለው በመናገር ላይ ያሉቱ ጤናማ ናቸው? እኔ ጤናማ ስለመሆናቸው እጠራጠራለሁ በነገራችን ላይ አቶ ነአምን ዘለቀ ደህና ነው? በቀጣይ አደራዳሪ ሆኖ መምጣቱ የማይቀር ነው፤"መምጣቴ የማይቀር ነው" የሚለውን ዘፈን ጋበዝኩት
ለማንኛውም የመንግስት ባለስልጣናትን በስም ዝርዝር ይፋ አድርገው ሲገድሉና ሲያስገድሉ ከቆዩቱ ጋር መንግስት ቁጭ ብሎ የሚደራደርበት ሁኔታ ከአሁን በኋላ ሊኖር አይችልም! በአገር ክህደትና ሕገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ ከተንቀሳቀሱቱ ጋር መወያየት አይቻልማ!መንግስት ላድርገ ቢል እንኳ የሚፈቅድለት ህዝብ የለም
አሁን ከውስጥም ከሆነ ከውጭ ሆነው ተቀናጅተው የጠሉትን መንግስት በኃይል ለመገልበጥ ሙከራ ያደረጉ ቡድኖች ለሌላው ትምህርት መስጠት በሚያስችል ሁኔታ የእጃቸውን ማግኘት አለባቸው፤ቀደም ሲል ባቀረብኩት አንድ ፅሑፌ በውጭ የሚገኙ ረባሾች በኢንተርፖል በኩል ተይዘው ለሕግ መቅረብ እንዲችሉ መንግስት መስራት እንዳለበት ለማሳሰብ ሞክሬ ነበር አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል  ጋር እየሰራን ነው ማለትም ትርጉም የለውም! https://yaadimedianetwork.blogspot.com/2023/04/blog-post_84.html

መንግስት በጥሩ ጅምር ላይ ይገኛል መልካም ጅምረ ነው፤አሁን የተጀመረው ጥረት ተመሳሳይ በቀጣይም እንዳይከሰት ሊያደርግ የሚችል ስለሆነ የመጨረሻው ውጤት እንስኪመዘገብ ድረስ ጠንክሮ መስራት ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ስልጣንና ኃላፊነት ነው!

Post a Comment

0 Comments