ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 26,2015 (YMN) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ያላቸውን የሁለትዮሽ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የጣሊያን መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ ቁርጠኛ እንደሆነ ማረጋገጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
0 Comments