የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ




ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 26/2015(YMN) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነትም የውጪ ማስታወቂያ ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ተወያይቶ አፅድቋል።
በውይይቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በክልሉ ከውጭ ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ እየተስተዋለ የሚገኙ ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ረቂቅደንብ ያግዛል።
በተለይም ደንቡ በክልሉ የውጭ ማስታወቂያን በአግባቡ ለመምራትና የሚስተዋሉ የተዘበራረቁ ስራዎችን ወጥ በሆነ መንገድ ለመከወን ያስችላል ብለዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ አክለውም የክልሉን የውጭ ማስታወቂያ ፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ተግባራዊ መሆን በሀረር ከተማ ከፅዳትና ውበት ጋር በተያያዙ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቀነስና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ለማሳደግ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
መስተዳድር ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በስፋት ተወያይቶ ከዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ሰራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ውሳኔ አስተላልፋል ሲል የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

Post a Comment

0 Comments