በአዲሱ ዓመት ፍቅርና አብሮነት እንዲሰፍን በትኩረት መስራት ይገባል- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ



ፊንፊኔ #Ethiopia መስከረም 01/2015(YMN) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ2016 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

በመልዕክታቸውም÷ ዓመቱ የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅና የይቅርታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
አዲሱ ዓመት አዲስ እይታና አስተሳሰብ እንዲሁም የተሻለ እንድንሠራ ቃል ለመግባት ተጨማሪ እድል የሰጠ በመሆኑ በአግባቡ ልንጥቀምበት ይገባል ብለዋል።
ትውልዱ ሀገርን በአብሮነት ካጸኑ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ትምህርት በመውሰድ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሰላም መስራት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Post a Comment

0 Comments