በብልፅግና ዘመን ስልጣንን በግርግር ማግኘት እንደማይቻል ዳግም ታይቷል!

 



ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 06,2015(YMN) የኢህአዴግ አስተዳደራዊ ዘይቤ ተገርስሶ የብልፅግና ፓርቲ ራሱን ለማደራጀት ሙከራ በጀመረበት ሰሞን ማስፈራራት በሚመስል መልኩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ በመፈላለግ የተሰባሰቡ ፅንፈኞች ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም እያሉ በመጮህ ጆሮአችንን ሲያደነቁሩን ቆየተዋል

በአሜሪካ የሚገኙ የታክሲ አሽከርካሪዎችም በእነ እንቶኔ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረውላቸው “የፌዴራሊስት ኃይል” በሚል ስያሜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ስልጣን ላይ ጉብ ለማለት ቅድመ ዝግጅት አድርገው እንደነበር በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ስናስታውስ ሽር ጉዱ አስቂኝ እንደነበር መቼም ቢሆን የምንዘነጋው አይሆንም

ቀደም ሲል በሰኔ 16 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላይ ቦምብ  በማስወርወር የግድያ ሙከራ አድርጋ ያልተሳካላት ወያኔ ከዚያ በኋላ በድግግሞሽ የፈጠረችው ግርግርና ዳግም ስልጣን ሙከራ ወደምትወደው ስልጣን ሊመልሳት አልቻለም

ወያኔ ከአገር የዘረፈችውን ገንዘብ መድባ ከየአካባቢው የተለቃቀሙ ወሮበላ ቦዘኔዎችን በማሰማራት ዜጎች በተለያዩ ክልሎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ በማድረግ “አብይ አገር ማስተዳደር አልቻለም ኢህአዴግ ይሻለናል”ለማስባል ያልፈነቀለችው ድንጋይ አልነበረም፤ደግሞም የፈለገችውን አስብላ አንዳንዶችን  ሰምተን ታዝበን አልፈናል

ከዚህ ሙከራ በኋላም በተፈጥሮዋ ጫና ምክንያት አርፋ መቀመጥ ያልቻለችው ወያኔ የማይደፈረውን የሰሜን ዕዝ  ደፍራ ወደ ስልጣን ኮርቻ ለመመለስ ያደረገችው ጥረት መቼም ቢሆን ሊረሳ የማይችል ጠባሳ ፈጥሮባት በማለፍ ወዳ ሳይሆን ተገዳ ወደ ፕሪቶሪያና ናይሮቢ የሰላም ስምምነት እንድትመጣ በማድረግ ትጥቋን እንድትፈታ አስገድዷታል፤አሁን ባለው ሁኔታ የሰላም ስምምነት ተፈርሞ ወደ ዘላቂ ሰላም ጉዞ እየተደረገ ቢሆንም ይህን እውነት መካድና አለማንሳት አይቻልም!

በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ወያኔ ተሽመድምዳለች፤ከአሁን በበኋላ ወደ ስልጣን የመመለስ አቅም የላትም ብሎ ያመነ ሌላ ኃይል ደግሞ ከሰሞኑ የሃይማኖትን ጉዳይ ተገን በማድረግ በመንግስት ግልበጣ ወደ ስልጣን ለመመለስ እንቅስቃሴ ጀምሮ ሙከራው መክሸፉን በተግባር አየን

ይህ ኃይል ከቀድሞ አባቶቹ የወረሰው”የእኔ አውቅልሃለሁ’ በሽታ የተጠናወተው የቡርዣ ስብስብ መሆኑን በድርጊቱ አይተናል፤ራሱን በከፍታ ላይ በማስቀመጥ ሌሎችን በመናቅ የሚታወቀው ይህ ቡድን በጫጫታ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ ለማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ በመረጋገጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እንደተለመደው በጥበብ ከንቱ ሙከራቸው እንዲከሽፍ ማድረግ ችሏል

ይህ የአማራ ፅንፈኛ ቡድን በውይይት መፍትሄ ማግኘት የሚችለውንና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በመጠቀም በአቋራጭ ወደ ስልጣን ለመምጣት ሙከራ ማድረጉ የሚገርም ሊሆን አይችልም፤ቡድኑ ማድረግ የሚችለውን ሙከራ ነው ያደረገው፤በሃሳብ የበላይነት በምርጫ በመወዳደር የህዝብን ልብ ገዝቶ ወደ ስልጣን መምጣት የማይችል ኃይል ማድረግ የሚችለው ያደረገውን ሙከራ ብቻ ነው

ኢትዮጵያ አሁን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በሚገኝ ጠላት ልትደፈር የማትችል አገር መሆን ችላለች፤ጠላቶቿን እንዴት በመመከት መመለስ የምትችል ድንቅ አገር መሆኗን ለተደጋጋሚ ጊዜ ማሳየት የቻለች አገር ሆናለች፤እናም በብልፅግና ዘመን የተለያዩ ምክንያቶችን ተገን በማድረግ በብልፅግና ዘመን በግርግርና ጫጫታ ስልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረጋገጧል!በዚህ እውነት ከየትኛውም ብሔር የሚወጣ ፅነፈኛ ተስፋውን በመቁረጥ በሰላማዊ ሁኔታ ብቻ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል!

Odeeffannoo dabalataa iddoo jirtanitti kanneen irraayis dubbisaa:

Blog:https://yaadimedianetwork.blogspot.com/

Facebook page:https://www.facebook.com/Yaadimedianetwork

Twitter:https://twitter.com/Qaroomina

Telegram:https://t.me/yaadimedianetwork

https://www.instagram.com/yaadimedianetwork/

Linkdein:https://www.linkedin.com/in/yaadimedia/

Pinterest:https://www.pinterest.com/Yaadimedia/

You tube:https://www.youtube.com/channel/UCFslwPKDM0QxVrt75_p_kuw

Tik Tok:https://www.tiktok.com/@yaadimedia1/

 

 

Post a Comment

0 Comments