ፓስተር ቢኒያም ምን እያሉ ነው?



ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 05,2015(YMN) እርስዎ 33 ጠበቆች የቆሙልዎት ሰው እንደሆኑ ከሰሞኑ እርስዎን የሚያንቆለጳጵስዎት አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ሰምቻለሁ
ትናንት በአንድ የዱርዬ ማህበራዊ ዩቱበር ሚዲያ ላይ ቀርበው ያስተላለፉት መልዕክት ለዳግም እስር በር የሚከፍትልዎት እንደሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው
እርስዎ የኢትዮጵያ መንግስት ትዕቢተኛ ነው ብለዋል፤ሌላው ቀርቶ ይህ አገላልፅዎ ብቻ በሕግ የሚያስጠይቅዎት ነው
በኢትዮጵያችን ከእስር ቤት የተለቀቁ ሰዎች ጀግና ነኝ ማለታቸው ያሳዝናል ያስገርማልም! ጀግና ስለሆኑም ከጽንፈኛ ዳያስፖራዎች ገንዘብ እየተዋጣልዎ ወደ ባለቤትዎ የባንክ አካውንት ገቢ እንደሆነ ነገሩን እንኳን ደስ አለዎት! ነገር ግን ወደ ራስዎ የባንክ አካውንት ለምን አልገባም? መቼም ባልና ሚስት አንድ አካል አንድ አምሳል ስለሆኑ ይሉኝ ይሆናል፤ይሁን በሰበቡ ሃብት እየሰበሰቡ ነው ማለት ነው
የሃይማኖት አባት፤የእግዚአብሔርን ቃል የሚያውቅ ሰው እንዲህ እርስዎ እያደረጉ እንዳሉት የሚያደርግ አይመስለኝም የእግዚአብሔር ቃል "ትዕቢት ጥሩ አይደለም" ይላል #Ethiopia #RuleOfLaw


Post a Comment

0 Comments