ካራማራም ከአድዋ ጋር እኩል ነው!





ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 26,2015(YMN) አንዳንድ ወዳጆቼ በውስጥም ሆነ ፊት ለፊት በሰጡኝ አስተያየቶች በአማርኛ ቋንቋ መፃፍ መቀጠል ይኖርብሃል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የምታጋራንን መልዕክቶች በአፋን ኦሮሞ ብቻ ከፃፍክ እኛን ታጣለህ ብለውኛል
በእርግጥ ወዳጆቼን ማጣት ለእኔ ጉዳት ነው በሚል ምክንያት ቀደም ሲል ያጋራሁት የጥንቃቄ መልዕክት እንደተጠበቀ ሆኖ የሌላውን መብት ሳልነካ የራሴንም ሳላስደፍር ልክ እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋዬ አፋን ኦሮሞ በምወደው የአማርኛ ቋንቋም መልዕክቶቼን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማጋራት አስፈላጊ እንደሆነ መወሰኔን እየገለፅኩ አስተያየትና ምክረ ሃሳብ ለሰጣችሁኝ ወዳጆቼ ሁሉ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ!
በዚሁ ስቀጥል እንኳን ለ45ኛው የካራማ የድል በዓላችን አደረሳችሁ!
እኔ የምለው ይህ አኩሪ የድል በዓላችን አዲስ አበቤዎችን አይመለከትም እንዴ?
የድል በዓሉ በተከበረበት ቦታ የዘማች ቤተሰቦችና የተሰወኑ አካላት ብቻ መገኘት አለባቸው ያለው ማነው?
የካራ ማራ ድል መታሰቢያ በዓላችን ከአድዋ ድል መታሰቢያ በዓላችን ጋር በእኩል ደረጃ መታየትና መከበር ይገባዋል!
ከዚህ ጋር ተያይዞ የገረመኝ ጉዳይ አለ፤በ127ኛው የአድዋ ድል በዓል የተመለከትናቸው ወጣቶች በተመሳሳይ ሁኔታ በካራ ማራ 45ኛ ዓመት የድል በዓል ላይ ለምን አልተገኙም? ብዬ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ፤"ጠርጥር ከገንፎ አይጠፋም ስንጥር"የሚል አባባልም ትዝ ብሎኛል
የአድዋ ድል በዓል የአፄ ምኒሊክ ስም ጎላ ብሎ የሚነሳበት በመሆኑ ምክንያት ከሆነ ስህተት ነው፤ሁለቱም ድሎች በወራሪዎች ላይ የተጎናፀፍናቸው አኩሪ ድሎች ስለሆኑ በእኩል ደረጃ መታየት አለባቸው
ለማንኛውም ምኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው እያላችሁ ስታጓሩ የምትውሉ ቡድኖች ምኒሊክ በጊዜው ንጉስ ነበር ዛሬ ግን ንጉስ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ የለም እውነቱን እወቁ!
ወጣት ወገኖቼ ቆም ብላችሁ አስቡ ከአዲስ አበባ ውጭ በመምጣት መንግስትን እገለብጣለሁ ብሎ በቅዥት የሚንቀሰቃስ ኃይል የለውጡ መንግስት እርምጃ መውሰድ ሲጀምር የሚሸሽበት ቦታ ያለው ነው ፈርጥጦ ድራሹ የሚጠፋ ነው ልክ ሰሞኑን እንድተመለከትነው ማለት ነው
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ወጣቶች ግን የትም የምትሸሹበት ቦታ የላችሁም
ይህን እውነታ በመረዳት ከአጥፊ ኃይሎች ሴራ ራሳችሁን ብትጠብቁ መልካም ነው የሚል ምክረ ሃሳብ ልሰጣችሁ እወዳለሁ 

Post a Comment

2 Comments

  1. Thank Bire for valuable information sharing us and reconsidering your stand based on your friends'comments.

    ReplyDelete