እናንተ የምትሿት ኢትዮጵያ የለችም ልትኖርም አትችልም!

 



You should know the fact!

ፊንፊኔ  #Ethiopia መጋቢት 01 2015(YMN) "ጅብ የማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ" ይላል አሉ የዚያ አይነት ነገር ነው የዳያስፖራ ድርጅቶች ስለ ኢትዮጵያ ያስባሉ እንዴ ለካ?ለመሆኑ እነርሱ የሚፈልጓት ኢትዮጵያ አሁን አለች ወይ?በቃ ተደራጅታችሁ ለኢትዮጵያ ሰራችሁ ማለት ነው? እናንተ የአማራ ጽንፈኛ ኃይል መፈልፈያ ኢንኩቤተር መሆናችሁን አታውቁም እንዴ? ይህ እውነት ከተደረሰበት ቆይቷል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን እንዲያድርግላችሁ ነው ደብዳቤ የፃፈችሁለት?ለማስጨነቅ ነው ወይስ ለማሸማቀቅና ለማስጠንቀቅ? ይግረማችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለው ድጋፍ እጅግ በጣም ጨምሯል
የመታወቂያ ሎጎ በማዘጋጀት ያለችሁ ለማስመስል ትሞክራላችሁ እንጂ የሌላችሁ የዳያስፖራ ድርጅቶች እንደሆናችሁ እናንተን በተመለከተ የወጡ መረጃዎች እያሳዩ ነው መረጃዎቹ እንዳረጋገጡት እናንተ በስም የገዘፋችሁ ልክ እንደ አንዳንድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁለት ወይም ሶስት ቢበዛ አምስት አባላት ይዛችሁ ጉራ የምትነዙ መሆናችሁ ተደርሶበታል
በእርግጥ ከአምስት አመታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች መጥቶ ታሪካዊ ንግግር ባደረገላችሁ ጊዜ የሰነቃችሁት ተስፋ ሲመናመን መባነናችሁ ታውቃል
የምትሰሙት ራሳችሁ መስማት የምትፈልጉትን ብቻ ስለሆነ ወይም አልገባችሁም ይሆናል እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኮ በወቅቱ አንድነት "አንድ አይነትነት አይደለም" በማለት እንቅጩን ነግሯችሁ ነበር
ይህን እውነት ተረዱ እስኪ፤ ተውን! እናንተ ሁለተኛ አገር አላችሁ እኛ ደግሞ አንዲት አገር ኢትዮጵያን ብቻ አለን በውድ አገራችን ኢትዮጵያ በሰላም መኖር እንድንችል ብትተውን ይሻላል አይ "ባልበላውም ልጫረው"እንዳለችው እንስሳ ከሆናችሁ ደግሞ አትችሉም ብለናል! እኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ነን!

Post a Comment

0 Comments