የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ የዳያስፖራ ማህበሰረብ ድርጅቶች ፃፉት ለተባለው ደብዳቤ በራሴ አተያይ ምላሽ በሚመስል መልኩ አራት ነጥቦችን የያዘ መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ዛሬ አስተላልፈው ነበር
ይህን መልክዕክት ያገኘው ፅንፈኛ ዩቱበር ደረጀ ሃብተወልድ ክቡር ሚኒስትሩን እየዘለፈ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትን ለመቀስቀስ ሞክሯል
ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት አጠቃላይ ለውጡን የተመለከቱ ጉዳዮች የዳያስፖራ ድርጅቶችም ሆኑ ዳያስፖራው ለለውጡ ቀጣይነት የበኩላቸውን ሚና ማበርከታቸውን አሁንም ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙና አንዳንድ ትክክል ያልሆኑ አካሄዶች ግን መታረም እንዳለባቸው ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅበት በትህትና የሚጠይቅ ነው
0 Comments