ፊንፊኔ #Ethiopia ሰኔ 02/2015(YMN) ንብና ዝንብ በቅርጽ ይመሳሰላሉ፡፡ግብራቸው ግን ለየቅል ነው፡፡ንቦች የሚበሩት ጣፋጭ መአዛ ወደሚሸታቸው የአበባ ቦታ ነው፡፡ዝንቦች የሚከንፉት ግን የሚሰነፍጥ ሽታ ወዳለው ቆሻሻ ቦታ ነው፡፡ንቦች ጠፋጩንና ለሰው ልጅ ጤንነት ተስማሚ የሆነውን ማር የሚሰሩበትን ንጥረ ነገር ቀስመው ይመለሱና ማሩን ይሰራሉ፡፡ዝንቦች ግን ቆሻሻ ዘግነው በመምጣት የሰውን ጤንነት ይበክላሉ፡፡
ማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ዩቲዩብ ላይ የተጣደው አብዛኛው የሁከት ነጋዴ እንዲህ ነው፡፡የሀገርን ክብር የሚነካና የህዝብን ሰላም የሚያናጋ ቆሻሻ እየለቃቀመ ሀገሩን ሲያዋርድና ሲያሳንስ መሽቶ ይነጋለታል፡፡ይህ ቆሻሻ ቃራሚ መንጋ እንደልማዱ አሰፍስፎ የጠበቀውን ወሬ ግን ዛሬ መስማት አልቻለም፡፡
ጨዋዎቹና ሰላም ወዳዶቹ ሙስሊም ወንድሞቻችን የሀይማኖት አባቶቻቸው ያስተላለፉላቸውን መልዕክት ተቀብለው የዛሬውን የጁምአ ሶላት በሰላም አካሂደዋል፡፡እናም በስማቸው ነግዶ ሊያተርፍ ያሰፈሰፈው የዩቲዩብ ነጋዴ ሁላ ማረፊያ ቆሻሻ አጣ!!ከባድ መርዶ!! እነዘዚህ የደም ነጋዴዎች ሙስሊም ወገኖቻችንን እንደማይወዱ ሰሞኑን በለቀቁት አስነዋሪ የቪዲ መልዕክታቸው አረጋግጠዋል፡፡ግን ደግሞ መንጋው ሌላ ቆሻሻ ፈልጎ ያገኘ ይመስላል፡፡
በኢትዮጵያ መከላከከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረው አልሸባብ ያሰበውን ሳይፈጽም መደምሰሱን መከላከያ ሰራዊታችን በማስረጃ አስደግፎ ቢገልጽም እነሱ ግን የሶማሊያውን አሸባሪ ቡድን አልሸባብን አምነው ‘’ የኢትዮያ ሰራዊት በአልሸባብ ጥቃት ደረሰበት‘’ብለው የልባቸውን መሻት በደስታ ስሜት ነገሩን፡፡
ይህን ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡መቼም ሰው መንግስትን ሊጠላ ይችላል፡፡ቢጠላና ቢቃወምም ኃጢአትም ወንጀልም አይደለለም፡፡ነገር ግን ከመንግስት ይልቅ ጠላትን ያውም አሸባሪ ቡድንን አምኖ የኢትዮያን ጀግና የመከላከያ ሰራዊትን ለማሳነስ መሞከር የለየለት የሀገር ክህደት ወንጀል ነው፡፡
በዚህ በደምና በአጥንቱ ኢትዮጰጵያን እያስከበረ ያለን የሀገርና የሕዝብ ሰራዊት ክብር መንካት ከክህደት ሁሉ የከፋው ቀይ መሰር ነው፡የዩቲብ ሆድ አደሮች የአንዋር መስጊዱ የሁከት ጉጉታቸው ቢከሽም ወደ ሌላ አዲስ የቆሻሻ ዛፍ ለመንጠላጠል እየሞከሩ ነው፡፡ከትህነግ ጎን ወግኖ ኢትዮጵያንና መንግስቷን እየፈተናት የሚገኘው የአሜሬሪካ መንግስት/USAID ለኢትዮያ እርዳታ አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ ጮቤ ሲረግጡ ይሰማል፡፡
ምክንያታቸው ግልጽ ነው፤ኢትዮጵያ ስንዴ አምርታ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ ያሳደረባቸውን ቁጭት ለመበቀል ሲሉ ነው፡፡ሌላ ትዝብት አተረፉ እንጂ ኢትዮያ እንደሆነች እንደልማዷ ይህንንም ትሻገረዋለቸ፡፡የቀድሞ ኢሳት ተረፈ-ምርቶችና የነአመን ዘለቀ ቡችሎች እንደአሜባ ተበጣጥሰው በየዩቲዩባቸው የሚመኙት ክፉ ምኞት መክሸፉ የማይቀር ነው፡፡እስከዚያው በነእንቶኔ ጀግና ጀግና ተረታቸው ይጸናኑ፡፡
(በዓለምነው አበበ)
0 Comments