ፊንፊኔ #Ethiopia መስከረም 11/2016(YMN) በአማራ ሕዝብ ስም ተገዝተው “በጥቂት ቀናት ውስጥ አራት ኪሎ እንገባለን” በማለት ለተከታዮቻቸው ባዶ
ተስፋ የሞሉቱ ዛሬ የታሉ? እኔ እምለው እዚህ ፊንፊኔ ተቀምጠው ፋኖ ይመጣል ብለው ተስፋ ያደረጉቱ ብጥል ናቸው ወይሰ ሞኝ?
እኔ ጠቅላዩ ቀደም ሲል እንዳሉት ጅል ጅላጅልና ጅላንፎ ናቸው ብያቸዋለሁ
ለመሆኑ ክፍፍሉ እንዴት ነው? “አንዱ ከህዝባዊ ግንባር በስተቀር ፋኖ በውጭ አገር ሌላ ወካይ የለውም
ሲል ሌላው ተነስቶ አንድ የፋኖ አመራር ውጭ አገር ለሚገኙ ሁለት አካላት ቃል ይገባል”ብሎ ነግሮናል
“የአማራ ትግል የመጨረሻው ጡዘት ላይ ደርሷል” ብለው ሲያቅራሩና ሲፎክሩ ከሰነበቱ በኋላ ከሰሞኑ
መከፋፈላቸውን በአደባባይ ወጥተው አስረድተውናል ምናልባት ሴራም ሊሆን ይችላል “ጠርጥር ከገንፎ አይጠፋም ስንጥር”
ለማንኛውም አሁን ያለው ሁኔታ በጣም ጥሩ ነው!መልካም ነው! ለአማራ ሕዝብ የመጣው መከራና እንግልት
ወደ አክራሪ ጽንፈኞች ተመልሶ እየሄደ ነው ርቦናል የሚሉም እንዳሉ ተሰምቷል እንግድህ ትግል ከተባለ ረሃቡንም ችሎ ነው በርቱ!፤ይህ
አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ለአማራ ክልል ነዋሪዎች ትልቅ ብስራት ነው፤ከአሁን በኋላ በሚነዛው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ዶላር
የሚያዋጣ ዳያስፖራ አይኖርም ወይም ይቀንሳል
በጽንፈኛ ቡድኖች መካከል አሁን የተፈጠረው ክፍፍል ያለ ምክንያት የመጣ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፤የግንኙነቱ
መሰረት ስልጣንና ጥቅም በመሆኑ በቀጣይም ጥቅም የሚጎድል መሆኑ ሲታሰብ ወደ መከፋፈል፤መሰዳደብና ማስጠንቀቂያ መስጠት መግባት
ግዴታ ሆነ፤ያው ወሮ በላ ሌባ ሲሰርቅ እንጂ ሲከፋፈል አይስማማም እኮ!
ሌላው የክፍፍላቸው ትልቅ ምክንያት በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን መሬት ላይ የተሰራው ተጨባጭ ስራ
ነው፤አይነያገሯትም እንጂ በደንብ ተደቁሰዋል በጀግናው ሠራዊታችን መስዋዕትነት በአማራ ክልል የሕግ የበላይነት ተከብሯል፤አስጊ
ሆኖ የመጣው የእልቂትና የፍጅት ድግስ በአስተማማኝ ሁኔታ ተቀልብሷል ተመክቷል
በዚህ ውጤት ላኪዎቻቸውም መደንገጣቸው እውነት ነው፤የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እኮ መጥተው ፊት ለፊት
አይዋጉንም የእኛን ባንዳና ሆዳሞች ቀጥረው ይልኩብናል እየሆነ ያለውም ይኸው ነው እውነቱን እንገንዘብ!
0 Comments