ኢትዮጵያ በዕድገት ግስጋሴ ላይ ትገኛለች የዕድገት ግስጋሴዋን ወደ ኋላ መመለስ የሚችል አንድም ኃይል እንደሌለ ተረጋግጧል መሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይህን እውነት በርካታ ጊዜ ደጋገመው ተናግረዋል
መጪው ጊዜ ብሩህ ነው አይናችንን ከፍተን ማየት ከቻልን ደግሞ ማረጋገጫዎቹ በርካታ ናቸው የህዳሴ ግድባችን ግንባታ ከ93 በመቶ በላይ ደርሷል ሊጠናቀቅ ነው፤ታላቁ ግድባችን ግንባታው ሳይጠናቀቅም የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፤ግብፅም በመጨረሻው የሶስቱን አገራት በአባይ የመልማት ፍላጎት አከብራለሁ ብላለች በቁርጠኝነታችን የተገኘ ድል ነው!
ታላቁ ግድባችን ግንባታው ሲጠናቀቅ የአሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኙ በጨለማ እየኖሩ ያሉ ዜጎች ሁሉ አገልግሎቱን በተሟላ ሁኔታ የሚያገኙ ይሆናል ኢትዮጵያም በኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽያጭ በምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ታድጋለች ትመነደጋለች
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ግብርናችንም እንዲዘምን እየተሰራ ነው አርሶ አደሮቻችን በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጆዎች መጠቀም ጀምረዋል እንደ ድሮ በበሬ ብቻ ማረስ በሂደት የሚቀር ይሆናል፤በግብርናው ዘርፍ ውስጥም ግብአቶችን በመሰወርና በህገ ወጥ መንገድ መክበር የሚሹ ሌቦች ቢኖሩም የአርሶ አደሩ ምርታማነት ተስፋ ሰጪ ሆኗል
አርሶ አደሮች በቡድን ተደራጅተው በክላስተር እርሻ ላይ ተሰማርተዋል ተጨባጭ ለውጥም እያገኙ መሆናቸውን በሚሰጡት አስተያየት እያረጋገጡ ነው፤የአርሶ አደሩ ስኬት፤ምርትና ምርታማነት መጨመር ደግሞ ለከተማ ነዋሪውም ትልቅ ተስፋ ነው
አሁን በተለይ በከተማ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ጊዜያዊ ነው በንግድ ስርዓቱ ላይ ያለው መበላሸት የፈጠረው ነው፤በዋጋ ንረት ምክንያት ሕዝብ መንግስትን እንዲያማርር የውስጥና የውጭ ጠላት በመቀናጀት የሚፈጽመው ሴራ እንዳለም መዘንጋት አይገባም
በአንዴ መክበር የሚሻው ስግብግብ ነጋዴና ደላላው ተቀናጅቶ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ይታወቃል፤ይህም ጊዜያዊ ችግር ነው ያልፋል፤አሁን በሴራና ተንኮል መንግስትን ከስልጣን ማውረድ አይቻልም!ሁሉም ጊዜ አለውና በጫጫታ፤ህዝብ አገልግሎቶችን እንዲያጣ በማድረግና ስራ አጦችን አደራጅቶ ጫካ በማስገባት የትጥቅ ትግል በማካሄድ መንግስትን ከስልጣን ማውረድ የሚቻልበት ሁኔታ የለም
አገር ሰላም ነው አማን ነው! በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ያሉ ሽፍቶች በተላላኪነት በአንዳንድ አካባቢዎች የሚፈፅሙት ድርጊት ሰላም የሌለ ቢያስመስልም አገር ሰላም ነው
የኢትዮጵያን ሃብት ዘርፎ ሲያስዘርፍ የኖረው ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት ተሽመድምዷል፤የወያኔን ፈለግ የተከተለው ጃውሳም አቅመ ቢስ መሆኑ ተረጋግጧል የሕዝብ ተቀባይነት የለውም፤የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በሰላም መኖር እንደሚሻ በተጨባጭ ተግባሩ አረጋገጧል አገር ሰላም ነው!
0 Comments