የጽንፈኛ ኃይሎች ፍላጎትና ደጋፊዎቻቸው

 



ፊንፊኔ ታህሳስ 17/2016(YMN) የጽንፈኛ ኃይሎችን ፍላጎት፤አካሄድና የማፍረስ ሂደት ማወቅ፤መንቃትና መጠበቅ ኢትዮጵያን የሚወዱ ዜጎች ሁሉ ኃላፊነት ነው

ጽንፈኞቹ የትኛውንም ቀዳዳ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይሉ ቀደም ሲል በስፋት ተመልክተናል፤ለነገሩ ወጪት ሰባሪዎች ዕድል አያገኙም!እስከ አሁን ያደረጉት ጥረትና መፍጨርጨር ያስገኘላቸው ውጤት የለም
በሌላ በኩል የፅንፈኛ ኃይሎችን እኩይ ድርጊት አለመኮነን እና ዝም ማለት ጽንፎኞቹን ከመደገፍ የሚለይ አይደለም
ኢትዮጵያን የዘረፉ በህገ ወጥ መንገድ ሃብት ያካበቱ ለጽንፈኞች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩና በሁሉም ሁኔታ ለጽንፈኛ ኃይሎች ድጋፍ በማድረግ ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው
ምክንያቱም የታሪካዊ ጠላታችን ተላላኪ የሆኑ ጽንፈኞችን መደገፍና ምቹ ሁኔታ መፍጠር ለኢትዮጵያ ከማሰብ የሚመጣ አይደለም
ዘራፊው ባለሃብትና የተለያዩ ተቋማት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለጽንፈኛ ኃይሎች ድጋፍ የሚያደርጉት ለምንድነው? ብሎ መጠየቅ ይገባል!የትኛውም ሌባና ዘራፊ በህግ ፊት ቀርቦ መጠየቅን ይፈራል ያካበተው ሃብት ከመንግስት ሌባ ባለስልጣናት ጋር በመሞዳሞድ የተገኘ ሲሆን ደግሞ ተጠያቂነቱ የሚያሰጋ ነው
ስለዚህ ለጽንፈኛ ኃይሎች ከዘረፈው ላይ ድጋፍ በማድረግ ወደፊት ጉዳዩ ተጣርቶ በህግ ላለመጠየቅ ይፍጨረጨራል፤መንግስት እንዲፈርስለት ጽኑ ፍላጎት አለው ይህም በተለያዩ ወቅቶች በተግባር ታይቷል
ከዚህ ጋር ተያይዞ ተደርሶባቸው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉቱ ቤት ይቁጠራቸው ኢትዮጵያ ጠላቶቿን አንበርክካለች! ያለው ተጨባጭ እውነት ይህ ነው

Post a Comment

0 Comments