ፊንፊኔ ኢትዮጵያ ጥር
13,2015(YMN) በውድ አገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የሚከበሩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ከፍተኛ ድምቀት
የሚታይባቸው ናቸው፤የዘንድሮው የጥምቀት በዓልም እንደከዚህ በፊቱ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ተከናውነውበት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቅ
ችሏል፤ታቦቶች በሰላም ወጥተው በሰላም ተመልሰዋል እስከ ዛሬ ድረስ በማደሪያቸው ቆይተው ዛሬ የተመለሱ ታቦቶችም በሕዝብ ታጅበው
ገብተዋል
ለዘንደሮው ያደረሰን
ፈጣሪችን በቀጣዩ ዓመትም ደማቅና ሰላማዊ የጥምቀት በዓል ለማየት ያብቃን!የከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም ማለፍ የቻለው
በእግዚአብሔር ጥበቃ፤በፀጥታ ኃይሎችና በመላው ሕዝብ የጥንቃቄ ክትትል እንደሆነ መረዳት ይገባል
የመንግስት ኮሙኒኬሽን
አገልግሎት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ አካላት ሁሉ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ምስጋናውን አቅርቧል
ተገቢ ነው!
በዓሉ ምንም ነገር
ሳይፈጠር ኮሽታ ሳይሰማ በሰላማዊ ሁኔታ ማለፍ መቻሉ የሚያስቆጫቸውና የሚያበሳጫቸው የያዙት የጥፋት ዕቅድ የከሸፈባቸው ኃይሎች
እንዳሉ እናውቃለን ይህን መዘንጋት አይገባም
ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ
በዓላትን ተገን በማድረግ በሚፈጥሩት ግርግር ተቀባይነት ለማግኘት የሚሯሯጡ ኃይሎች ዘንድሮ አልተሳካላቸውም፤ምክንያቱም ሕዝብ ፊት
ነሳቸው የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በመቀናጀት የሚጠበቅባቸውን ስራ አከናወኑ፤በመሆኑም ሴረኞች ከሸፉ!ኢትዮጵያ ደግሞ ደስ አላት
በበዓሉ ዋዜማ ላይ የብሔራዊ
ደህንነት ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ ተልዕኮ ተቀብለው የበዓሉን ሂደት ለማወክና የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የተዘጋጁ ቡድኖች
እንደነበሩ አረጋግጧል
በተለይም ወደ ከተማ
የገቡ የኦሮሞና አማራ ሸኔ ፅንፈኛ ቡድን አባላት የሆኑ 371 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውና ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር
መሳሪያዎችም እንደተያዙ የግብረ ኃይሉ መግለጫ ይፋ አድርጎ ነበር
0 Comments