ከትናንት ጀምሮ የሃይማኖትን ጉዳይ እያነሱ ፅንፍ የወጣ ክርክር
የሚያደርጉ፤በሚሰጡት አስተያየትም መሪዎችና ግለሰቦችን የሚዘልፉ በተለይም በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በግልፅ ሲሳደቡ፤ሲያዋረዱ፤ግጭት
ቀስቃሽ ንግግሮችን ሲያደርጉ እየተሰማ ነው
የዚህ ዓይነት አካሄድ ማንንም ተጠቃሚ ሊያደርግ አይችልም
‘ሕገ ወጥ ድርጊት ፈፅመዋል’እየተባሉ ያሉ አባቶች በያዙት
አቋምና አካሄድ ስህተት ፈፅመው ሊሆን ይችላል ላይሆንም ይችላል ለፈፀሙት ድርጊትና ላስተላለፉት ውሳኔ የራሳቸው ተጨባጭ መረጃና
ማስረጃ ሊኖራቸው እንደሚችል አምናለሁ
የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ
ማትያስም ተፈፀሟል በተባለው ድርጊት ምክንያት ለመፍትሔ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ ማስተላለፋቸው ለመግባባት ልዩነት እንዲፈጠር ያደረጉ
ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ ይችላልና መልካም ነው
መንግስት በጉዳዩ ገብቶ እርምጃ እንዲወስድ የቀረበው ጥሪ ግን
ፍፁም ስህተት ነው ይህ ፍላጎትና ጥያቄ እየተዳደርንበት ያለውን ሕገ መንግስት የሚጥስ ነው
ምናልባት ሕገ መንግስቱ ተቀድዶ መጣል አለበት ሲሉ የቆዩ ኃይሎች
ይህን አቋም ሊያራምዱ ቢችሉም እኛ በሕገ መንግስቱ ሕግጋቶች መሰረት በአገራችን በመኖር ላይ የምንገኝ ዜጎች ይህን አቋም መያዝ
አይጠበቅብንም፤አይገባም!
ምናልባት ሕገ መንግስቱን የሚጠሉ ወገኖች በሕገ መንግስቱ መሰረት
መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን አያውቁ ይሆን?ለማንኛውም በሕገ መንግስቱ መሰረት
1.መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው
2.መንግስታዊ ሃይማኖት አይኖርም
3.መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት
ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ይላል ይህን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 11 ስር ማየት ይቻላል
ለማንኛውም ለጠቅላላ ዕውቀት በ"አባ" ሳዊሮስ አማካይነት የተሾሙት እነዚህ ናቸው።
1."አባ" ገ/ማርያም ነጋሳ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
2."አባ" ተ/ሃይማኖት ወልዱ - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
3."አባ" ገብርኤል ወ/ዮሐንስ - ጉራጌ ሶዶ ሀገረ ስብከት
4."አባ" ገ/እግዚአብሔር ታደለ - ምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት
5."አባ" ሚካኤል ገ/ማርያም - ከምባታ ሀገረ ስብከት
6."አባ" ኃይሉ እንዳለ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
7."አባ" ተ/ማርያም ስሜ - ጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት
8."አባ" ኃ/ኢየሱስ መንግስቱ - ከፋ ሀገረ ስብከት
9."አባ" ወ/ኢየሱስ ኢፋ - ቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት
10."አባ" ጳውሎስ ከበደ - ሀዲያ ሀገረ ስብከት
11."አባ" ኃ/ኢየሱስ ተስፋዬ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
12."አባ" ገ/ኢየሱስ ገለታ - ሆሮ ጉዱሩ ሀገረ ስብከት
13."አባ" ጸጋዘአብ አዱኛ - ምሁር ኢየሱስ ገዳም "የበላይ ጠባቂ"
14."አባ" ኃ/ማርያም ጌታቸው - ምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
15."አባ" ወ/ጊዮርጊስ ኃ/ሚካኤል - ከሚሴ ሀገረ ስብከት
16."አባ" እስጢፋኖስ ገብሬ - ባሌ ሀገረ ስብከት ረዳት
17."አባ" ገ/መድኅን ገ/ማርያም - ጎፋ ባስኬቶ ሀገረ ስብከት
18."አባ" ኃ/ሚካኤል ንጉሤ - ጊኒር ሀገረ ስብከት
19."አባ" አብርሃም መስቀሌ - ዳውሮ,ኮንታ ሀገረ ስብከት
20."አባ" ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ - ምዕራብ ጉጂ ሀገረ ስብከት
21.አባ ኪ/ማርያም ቶሎሳ - ጅማና የም ሀገረ ስብከት
22."አባ" ወ/ማርያም ጸጋ - ቦረና ሀገረ ስብከት
23."አባ" አምደሚካኤል ኃይሌ - አርሲ (አሰላ) ሀገረ ስብከት
24."አባ" መርሐጽድቅ ኃ/ማርያም - ጌዴኦ,ቡርጁ,አማሮ ሀገረ ስብከት
25."አባ" ሞገስ ኃ/ማርያም - መናገሻ አምባ ቅድስት ማርያም ፣ ጋራ መ/ዓለምና ደ/ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ "የበላይ ጠባቂ"
26."አባ" ገ/ኢየሱስ ንጉሤ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
0 Comments