ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 07,2015(YMN) “ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን አትፈርስም” ይላሉ ክቡር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፤ለእሳቸው በተጨባጭ የታያቸው እውነት በመኖሩ ምክንያት እውነቱን ደጋግመው ሲናገሩ
ይሰማል “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፤በህይወቴ የሚያስደስተኝ ኢትዮጵያ ስትፈርስ ማየት ነው” በማለት በአደባባይ የለፈፉ ጥቂት
ገልቱዎች እንዳሉ ሁሉ ልክ እንደ ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የማትፈርስ አገር መሆኗን የሚያውቁ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያን
ውድ አገራቸውን ሊነቀነቅ በማይችል መሰረት ላይ እያስቀመጧት ነው
ለዚህ እውነት ተጨባጭ ማስረጃ የሚሆኑት የመንግስትን አቅጣጫ አምነው በመቀበል ክርምትና በጋ የተትረፈረፈ
የስንዴ ምርት እንዲኖር ጠንክረው በመስራት ላይ የሚገኙ በሚሊየን የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ናቸው
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የግብርና ስራ አብዮት ተወደደም ተጠላ የሚጨበጥ ውጤት እየተመዘገበበት
ነው፤በዚህ ለውጥ መመዝገብ የሚከፋቸው ኃይሎች ከውስጥም ከውጭም እንዳሉ ይታወቃል
በኢትዮጵያ ስንዴ ልማት ደስተኛ ያልሆኑ በአገር ውስጥ
የሚገኙ ኃይሎች እየተመዘገበ ያለውን አገራዊ ውጤት ምክንያቶችን በመደርደር ሲያጣጥሉ በውጭ የሚገኙ ኃይሎች ደግሞ “እኛ
የምንሰጣችሁ እርዳታ እያለ ምን አለፋችሁ” በማለት ወዳጅ ለመምሰል ምክረ ሃሳብ ሲሰጡ ተሰምተዋል፤ሁለቱም ኃይሎች በውሰጥም ሆነ
በውጭ የሚገኙቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው
አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ አሉ፤እነዚህ የጠላቶችን የተቀመመ ፕሮፓጋንዳ እንዳለ ቀብለው
የሚያራግቡ ናቸው፤በቅንነት የሚናገሩ በመሆናቸው የጠላቶችን ሴራ የተረዱ አይመስሉም
እናም ጠላት “በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ የስንዴን ምርት ለውጭ ገበያ መላክ
ለምን አስፈለገ? የዱቄት ፋብሪካዎች ስንዴ በማጣት በመቸገር ላይ እያሉ ስንዴን ኤክስፖርት ማድረግ አያስፈልግም” ብሎ ሲለፍፍ
የዋህ ኢትዮጵያዊያን ይህን በሴራ የተቀመመ ፕሮፓጋንዳ በመቀባበል ይናገራሉ
ሊታወቅ የሚገባው እውነታ በውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ጠላቶች ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት እንድታስመዘግብ
በፍፁም የማይፈልጉ መሆናቸው ነው፤ይህ ፍላጎታቸው ሊሳካ የሚችለው ደግሞ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ዜጎች ተስፋ እንዲቆርጡ
ለስራ እንዳይነሳሱ በማድረግ ስለሆነ ትኩረት ሰጥተው የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ እየተስተዋለ ነው
የስንዴ ፖለቲካ በዚህ መልኩ እየቀጠለ ቢሆንም ብልፅግና መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት የወራዶችን ፕሮፓጋንዳ
ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን ስንዴ ክረምት በዝናብ ውሃ፤በበጋ ወራት ደግሞ በመስኖ ውሃ በስፋት እንዲለማ በማድረግ ስንዴን ለውጭ
ገበያ በመላክ ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማግኘት
እንድትችል ማንኛውም ኃይል ሊቀለብሰው የማይችለውን ግስጋሴ በማድረግ ላይ ይገኛል
እውነት ነው! በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት እየጨመረ ይሄዳል፤በዚህ ምክንያት ታሪክ ስለተቀየረ የተቀቀለ የእርዳታ
ስንዴ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት ሁኔታ ሊፈጠር አይችልም!
የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ከአሁን በኋላ ከልካይ ቢመጣ እንኳ ስንዴን በኩታ ገጠም እርሻም ሆነ በግል ከማምረት
ወደ ኋላ ማለት አይችሉም፤ይህን ሁኔታ መፍጠር የቻለው የብልፅግና
መንገድ ብቻ እንደሆነ መረዳት ተገቢ ይሆናል!
በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ለምግብ እህል እጥረት ችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንም ካጋጠማቸው ችግር
መውጣታቸው የማይቀር ነው፤ድርቅ ድሮም ነበር ዛሬ አልተፈጠረም፤የፌዴራል መንግስትና የክልል መንግስታት በመቀናጀት የጀመሩት ጥረት
የተቸገሩ ዜጎቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አግኝተው በሂደት ራሳቸውን በመቻል ወደ ቀድሞው ሁኔታ በመመለስ ኑሮአቸውን መምራት ይችላሉ!
Odeeffannoo dabalataa iddoo jirtanitti kanneen irraayis dubbisaa:
Blog:https://yaadimedianetwork.blogspot.com/
Facebook page:https://www.facebook.com/Yaadimedianetwork
Twitter:https://twitter.com/Qaroomina
Telegram:https://t.me/yaadimedianetwork
Instagram:https://www.instagram.com/yaadimedianetwork/
Linkdein:https://www.linkedin.com/in/yaadimedia/
Pinterest:https://www.pinterest.com/Yaadimedia/
You tube:https://www.youtube.com/channel/UCFslwPKDM0QxVrt75_p_kuw
Tik Tok:https://www.tiktok.com/@yaadimedia1/
0 Comments