ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም ኖቤል ሽልማት ዳግም ቢኖርስ?

 

 



ሰላማዊ የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት እንዲኖር ቢፈለግም ከ20 ዓመታት በላይ የሚፈለገው ሰላም ሳይገኝ ቆይቶ ነበር፤ከአልጀርሱ የሰላም ስምምነት በኋላ የሰላምም ሆነ የጦርነት ሁኔታ ሳይኖር ቀርቶ በተለይም በድንበር አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ሰላማዊ ኑሮን እየናፈቁ ከሃያ ዓመታት በላይ የእንግልት ኑሮን ሲናፍቁ ቆይተዋል

ከአራት ዓመታት በፊት በብዙሃን ንቅናቄ በተለይም በኦሮሞ ቄሮዎች ትግል በአገራችን የመጣው ለውጥ የኢህአዴግ ቁንጮዎች በጉልበትና ሴራ ይዘውት ከቆዩት ስልጣን ለመውረድ ሲገደዱ አገር ወደ መምራት ስልጣን የመጡት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ የመጀመሪያ ስራቸው በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ ማድረግ ነበር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ባደረጉት ጥረት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም መውረድ እንዲችል አድርገዋል፤ቅድሚያውን ወስደው በድፍረት ወደ ኤርትራ በመጓዝ ከአገረ ኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመወያየት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ማድረግ ችለዋል፤በወቅቱ የነበረው አጠቃላይ ሁኔታ፤የሕዝብ ስሜትና የሰላም ፍላጎት ማስታወስ ተገቢ ይሆናል

ጠቅላይ ሚኒስትሩን እግዚአብሔርም ረድቷቸው በሁለቱ አገራት መካከል ሰላም ከወረደ በኋላ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትም የተጀመረ መሆኑ ይታወሳል

በወቅቱ “የሰላም ስምምነቱ ተቀባይነት የለውም” ዓይነት ፕሮፓጋንዳን መንዛት ተጀመረ ይህን ያደረገው “ከእኔ ፈቃድ ውጭ እንዴት ይሆናል!”በማለት የሚታወቀው ኃይል ሲሆን የሰላም ስምምነቱን በማጣጣል፤”በግለሰቦች መካከል የተደረገ ስምምነት ነው” “በኢሳያስና አብይ”እየተባለ ታሪካዊውን የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ዋጋ ለማሳጣት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ ነበር

ይህ ሁኔታ እያለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲወርድ በማድረጋቸው የዓለም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ መሆን ችለዋል፤የዶክተር አብይ አህመድ መሸለምም ሌላ ነገር ይዞ መጣ፤የአገር ውስጡ የአንድ ቡድን ተቃውሞ እንዳለ ሆኖ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልደ “ትራምፕ እኔ እያለሁ እንዴት የኢትዮጵያ መሪ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ይሆናሉ?”ብለው መጠየቃቸውን ሰማን

ምሁራን ነን ያሉ ከአገር ተሰደው በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ ቡድኖችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠው የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት እንዲነጠቅ ያላደረጉት ጥረት የለም ብዙ መፍጨርጨር ቢያደርጉም ጫና በማድረግ የተሰጠውን ሽልማት ማስነጠቅ ሳይችሉ ቀርተዋል

“ፍቅር፤ይቅርታ፤ሰላምና መደመር”ይሻለናል ብለው የአመራር ጉዞአቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በከሰሩ የፖለቲካ ነጋዴዎች በርካታ ጫናዎች ቢደረግባቸውም በመፍረስ አፋፍ ላይ ደርሳ የነበረችውን እናት አገር ኢትዮጵያን ከፍተኛ ትዕግስትና ጥበብ በተሞላ አመራራቸው ከመፍረስ አስከፊ አደጋ መታደግ ችለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወደ ሰሜን የመጡ ሰው ቢሆኑ ኖሮ በምን ያህል ደረጃ እንደሚጮህላቸውና እንዴት እንደሚንቆለጳጰሱ ይታወቃል፤በእርግጥ በለውጡ ጅማሮ ወቅት ላይ“የጎሳ ፖለቲካን ያጠፉልናል፤ሕገ መንግስቱን ቀዳደው ይጥሉልናል”ብለው ተስፋ ያደረጉ ወገኖች አድናቆታቸው ምን ያህል እንደሆነና በየመሃሉ የጠበቁት እነርሱ በሚፈልጉት እንዳልሆነላቸው ሲረዱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መርገም እንደጀመሩ ይታወቃል

አቋም የሌላቸው ቢንሸራተቱም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አመራር ምክንያት በጥቂት ዓመታት የተመዘገቡ ተጨባጭ ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦችን ተስፋ ያደረጉ፤ጊዜ ካገኙ እስከ አሁን ከሰሩት በላይ ለኢትዮጵያ ሰርተው ማሰራት የሚችሉ ብልህ መሪ መሆናቸውን የተረዱ ወገኖችም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ መሆናቸውን መካድ አይቻልም

ይህቺ ዓለም እውነተኛ ብትሆን ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ማግኘት የሚችሉበትን አስደናቂ ስራ ሰርተዋል

የትኛውም የኢትዮጵያ መሪ ማድረግ ያልቻለውን በቆራጥነታቸው ማድረግ የቻሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ግንባር በመዝመት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የውስጥም ሆኑ የውጭ ጠላቶች እንዲያፍሩ ማድረግ እንዲችል በጥበብ የተሞላ አመራር የሰጡ የምንጊዜም ድንቅ መሪ ናቸው

ከሰሞኑም ሰኔ 16 ቦምብ በማስወርወር የግድያ ሙከራ ካደረገባቸው ቡድን ጋር ፊት ለፊት ተቀምጠው መወያየት የቻሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠር ደጋፊ አላቸው!አጋጣሚውን አግኝተናል በማለት የስድብ ላንቃችሁን የከፈታችሁ ወገኖች እረፉ!ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም እንደቀድሞው ሆደ ሰፊ ሆነው አገርን የማስቀጠል ታሪካዊ ኃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛሉ

Post a Comment

0 Comments