በተለያዩ አገራት ትርጓሜ መሰረት የራሱ የሆነ ትርጉም ሊኖረው ይችላል፤በአገራችን አተያይና ሁኔታ መሰረት ግን ባንዳ ማለት አገሩን ክዶ ለሌላ አገር የሚሰራ ወይም ጥቅሙን ለማስከበር የሚንቀሳቀስ ቡድን ወይም ግለሰብ ማለት ነው፤በኢትዮጵያችን በተለያዩ ወቅቶች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለባዕዳን ያገለገሉ ለውጭ ኃይሎች የሰሩ ኢትዮጵያን ያቆሰሉ ባንዳዎች ነበሩ
ብዙ ጊዜ እንደምሳሌ የሚነሳው በአንድ ወቅት በማን አለብኝነት የጣሊያን መንግስት
ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ለጣሊያን አድረው የሰሩ መንገድ የመሩ አገር ሻጭ ባንዳዎች እንደነበሩ ይነገራል
በወቅቱ የነበሩ ባንዳዎች ኢትዮጵያ ጣሊያንን ድል በማድረጓ ሃፍረት ለመከናነብ
ተገደዋል፤ከዚያ በኋላ የተፈጠሩ ባንዳዎችም ተመሳሳይ ውርደት ደርሶባቸው አይተናል፤ሰምተናል
የሩቁን ትተን በቅርብ ጊዜ የተፈጠሩ ባንዳዎችን ድርጊትና መጨረሻቸውን ማየት
በጣም ጠቃሚ ነው የህወሃት/ኢህአዴግ ቁንጮ ባለስልጣናት የለውጡን አመራር በመቃረን ወደ መቀሌ ሄደው ከተሸሸጉ በኋላ በውስጥም በውጭም
ኢትዮጵያ እንድትጎዳ የሰሩ በርካታ ባንዳዎች በቅለው አይተናል
ከዚህ በኋላ የተፈጠሩ ባንዳዎች በውስጥም ሆነ በውጭ የፈፀሙት ድርጊት አገርን
ለመፍረስ አደጋ ያጋለጠ የዜጎችን ሕይወት የነጠቀና ንብረት እንዲወድም ያደረገ መሆኑን በተግባር እውን ሆኖ ተመልክተናል
አዳዲሶቹ ባንዳዎች ደግሞ የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያደርጉ የአስፓልት
መንገድ ላይ በመንከባለል ሲለምኑ አይተናል፤ልመናቸው ምላሽ ያገኘ
በሚመስል መልኩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከ11 ጊዜ
በላይ ተሰብስቦ መክሯል፤ይህም በታሪክ ተመዝግቧል
በመጨረሻም በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት
ጠንካራ ትግል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የተሸረበው ሴራ እነርሱ የሚፈልጉት ውጤት ሳይመዘገብ ተቀልብሷል፤የኢትዮጵያ አሸናፊነትም ተረጋገጧል
ይህ አኩሪ ውጤት ባዳዎችም ሆኑ ባንዳዎች ዳግም ውርደትን ለመከናነብ እንዲገደዱ
አድርጓል፤ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ለባንዶች ድጋፍ ወጪ ተደርጎ የተመደበው የገንዘብ ክፍያና የጦር መሳሪያ ባክኖ ቀርቷል
ከሰሞኑ በባንዳነት አገር እንድትጎዳ ተዘጋጅተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ቡድኖችም
ልክ እንደቀድሞዎቹ ባንዳዎች መክሸፋቸው የማይቀር ነው፤በተለይም የፅንፍ ሚዲያ ከፍተው በፅንፈኝነት በመቆም በለው ቁረጠው ገልብጠው
በማለት ላይ የሚገኙ ባንዳዎች ፍሪፋሪያቸውን ከመልቀም አልፈው ምንም ማምጣት የማይችሉ የቁራ ጩኸት በመጮህ ላይ የሚገኙ ናቸው
በፖለቲካ ገበያ የከሰሩ ፖለቲከኞችም በእነዚህ ፅንፈኛ ሚዲያዎች በመጠቀም ላይ
እንደሚገኙ መገንዘብ ተችሏል፤የሕዝብን ይሁንታ በማግኘት በምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲን አሸንፈው ወደ ስልጣን መምጣት ያልቻሉ አንዳንድ
ፖለቲካ እየሰራን ነው የሚሉ ደንቆሮዎች በዚህ ድርጊታቸው ማፈር ነው ያለባቸው!ለነገሩ እፍረትን የተለማመዱ በመሆናቸው ለእነርሱ
በመስራት ላይ የሚገኙት አዋራጅ ድርጊት ምንም አይመስላቸውም፤አያሳፍራቸውም እንዲያውም ይኩራሩበታል
ከሰሞኑ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረውን አጋጣሚ
በመጠቀም መንግስትን እንገለብጣለን ማለት ምን ማለት ነው?
በሕዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ ያለውን የኢትዮጵያ መንግስት በጉልበት ከስልጣን እናወርዳለን
ብሎ በድፍረት መንቀሳቀስ መነሻ ምክንያቱ ለመራጭ ሕዝብ ያላቸውን ከፍተኛ ንቀት የሚያሳይ ነው
በተለያዩ ምክንያቶች በአገር ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር ሰርግና ምላሽ የሚሆንላቸው
የከሰሩ ፖለቲካኞች አሁንም በንቀታቸው ተወጥረው የተካኑበትን ህዝብና
አገር የመበጥበጥበ ችሎታቸውን በተግባር ለማሳየት እየተፍጨረጨሩ የሚገኙበት ሁኔታን እየተመለከትን ነው
እርግጥ ነው እነዚህ ከንቱዎች እንደለመዱት የሚፈልጉትን ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉበት
ሁኔታ ፈፅሞ የለም፤ነገር ግን በሌሎች እሳት መያዝን የሚያውቁበት ስለሆኑ ሌሎችን በመገፋፋትና ለጉዳት በማጋለጥ ተረማምደው ወደሚፈልጉት
ስልጣን ለመምጣን ይንፈራገጣሉ፤ስልጣን የሚገባው ለእኛ ነው በማለት ሲለፍፉም እየተሰሙ ነው
የሃይማኖት አባቶች አለመግባባት እንደተለመደው በመወያየትና በመነጋገር ዘላቂ
መፍትሄ ማግኘቱ የማይቀር ነው ባዳዋችና ባንዳዎች ግን እንደለመዱት እፍረታቸውን ተከናንበው ይቀራሉ!
0 Comments