ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 01,2015(YMN) በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት የባለስልጣናት ቡድን በዚህ ሳምንት በአውሮፓ የተለያዩ አገራት የተሳካ የስራ ጉብኝት በማካሄድ ወደ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ተመልሷል
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ በሰጠው መረጃ እንዳስታወቀው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን የተሳካ ጉብኝት በማጠናቀቅ ወደ አገር ተመልሷል
በጉብኝቱ ከአገራቱ መሪዎች ጋር ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ ውይይቶች ተካሂደዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትናንተ እንደተናገሩት
በጣሊያን ሮም የተካሄደው ጉብኝት አገራችን የገንዘብ ድጋፍና ብድር እንድታገኝ ያስቻለ ነው
በዘሁ መሰረት የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ የ180 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተረጅም ጊዜ የሚመለስ
የገንዘብ ብድርም ፈቅዷል
በማልታ የተካሄደው ጉብኝትም ለልዑኩ የተደረገውን የክብር አቀባበል ጀምሮ የኢትዮጵያን ክብር ከፍ ያደረገና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይቶችን
ለማካሄድ ያስቻለ ነው፤በእርግጥ የኢትዮ ማልታ ግንኙነት በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ባይሆንም ጉብኝቱ የኢትዮ ማልታን ግንኙነት
ለማጠናከር የሚያስችል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል
ቀጥሎ በፈረንሳይ የተካሄደው የኢትዮጵያ መንግስት ልዑክ ጉብኝትም ቀደም ሲል በጦርነቱ ምክንያት በአውሮፓ ተፈጥሮ
የነበረውን ሁኔታ የቀየረና በቀጣይ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቬስትመንት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ መልዕክት የተላለፈበት
ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት በፈረንሳይ ፓሪስ
የአገሪቱን መሪ ኢማኑኤል ማክሮንን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ብለዋል
የኢትዮ ፈረንሳይ ግንኙነት ተጠናከሮ በመቀጠል ኢኮኖሚያዊ ውጤቶችን የሚያጠናክር እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ተስፋቸውን ገልፀዋል
በአጠቃላይ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ አሜሪካን ጨምሮ በተለያዩ አገራት የተካሄደው የሰላም ግንኙነት ኢትዮጵያ
ከተለያዩ ወዳጅ አገራት ጋር የነበራትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያደሰ በቀጣይም ለማጠናከር መሰረት የጣለ ነው ማለት ይቻላል፤ይህ
የኢትዮጵያ ስኬት እየተመዘገበ ያለው በክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አመራር መሆኑን መካድ አይቻልም!በአገር ውስጥ
በወቅታዊና በውይይት መፍትሄ በማግኘት በሚችል ክስተት ምክንያት ይህን ስኬት ማንኳሰስና ማጣጣል ነውር ይሆናል
0 Comments