የፌደራል መንግስት ከአሸበሪዉ “ኦነግ ሸኔ” ጋር ለመደራደር 10 ጊዜ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታዉቀዋል፡፡
ከሸኔ ጋር ለሚደረገዉ ድረድርም መንግስት ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥራ እንደገባ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተደረገዉ ድርድር ሙከራ ያልተሳካዉ የሸኔ ኃይል የተበታተነ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
መንግስት ከሸኔ ጋር ያለዉን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ ፍላጎት እንዳለዉም ተነስቷል፡፡
በቅርቡ የኦሮሚያ ከልል ለሸኔ ያቀረበዉ የእንደራደር ጥያቄ የክልሉ ዉሳኔ ሳይሆን የፌደራሉ መንግስት ዉሳኔ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማብራሪያቸዉ አንስተዋል፡፡
0 Comments