ጭቅጭቁ የሁለተኛውን አድዋ ድል እንዳያዘናጋን እንጠንቀቅ!

 

 

 



ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 22,2015(YMN) የ127ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23,2015 ዓ.ም በደማቅ ስነ ስርዓቶች ሊከበር ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቅቀዋል የዘንድሮው ልዩ ይሆናል ምክንያቱ በጣም ብዙ ስለሆነ መዘርዘር አያስፈልግም

ነግር ግን ዋና ዋና ምክንያቶችን መጥቀስ ተገቢ ይሆናል የዘንደሮ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መሪነት ደማቅ በሆነ ስርዓት የሚከበረው ኢትዮጵያ የተባበሩባትን ጠላቶች ያሸነፈችበት ማግስት ላይ የሚከበር በመሆኑ ነው የሚል ግምት አለኝ

የህወሃት ቡድን በማን አለብኝነት በስልጣን ዘመኑ ያካበተውን አቅምና የውጭ አጋሮቹን በመተማመን በህዝብ ትግል ያጣውን ስልጣን ዳግም ለመያዝ ያደረገው ጥረት በበርካታ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ድጋፍ ያገኘ ነበር፤ለህወሃት በመወገን ብዙዎች ከውስጥም ከውጭም ኢትዮጵያ እንድትንበረከክ በመረባረብ የሚችሉትን ሁሉ አድርገው አይተናል

የኢትዮጵያ ስም በዓለም መድረኮች ላይ ለተደጋጋሚ ጊዜ ባልተገባ ሁኔታ ተነስቷል፤ ዓለም አቀፍ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃኖች መርዘኛ ፕሮፓጋንዳቸውን ረጭተዋል፤በፊንፊኔ የሚገኙ የውጭ ዜጎችና ተቋማት ፊንፊኔን በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ ሳይታክቱ ግፊት አድርገዋል

ሁሉም ጠላቶች ያሰቡትና በኢትዮጵያችን ላይ የሸረቡት ሴራ ከግቡ ሊደርስ አልቻለም ከሽፎባቸው ከመንገድ ላይ ለመቅረት ተገደዱ፤ይህ አኩሪ ድል የተገኘው ለአገር በተሰው ጀግና የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ሌሎች የፀጥታ አባላት እንዲሁም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና በአጠቃላይም ቁርጠኛ የሆኑ የለውጡ አመራሮች በሰጡት ትክክለኛ አመራር ነው

በርብርብ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የመጡ ጠላቶችን በማሳፈር የተመዘገበው ድል ከ127 ዓመታት በፊት የጥንት ጀግኖች በአድዋ ላይ ከውጭ የመጣውን ጠላት በማንበርከክ ካስመዘገቡት ድል ጋር ተነፃፅሮ ሊታይ የሚችል ነው

በመሆኑም ይህን የቅርብ ጊዜ አኩሪ ድል በልባችን ይዘን 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በደማቅ ሁኔታ ማክበር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፤ፈተና የበዛበት የለውጡ አመራር የዘንደሮው አድዋ በዓል በመከላከያ ሰራዊት መሪነት እንዲከበር መወሰኑ ተገቢና አስፈላጊ ነው

ይህ ለምን ሆነ ብለው በአደባባይ የሞገቱትን አይተናል፤በተለይም በውጭ የሚገኙ አንዳንድ ኃይሎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የተካኑበትን የጥላቻ ትርክት ሲያሰራጩ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል፤እነዚህ ከቀድሞዎቹ ባንዳዎች የማይተናነሱ ባንዳዎች ናቸው፤አገር የላቸውም ፍርፋሪ በመለቃቀም ለመኖር የሚፍጨረጨሩ ናቸው አሁን ያለው የአገር አመራር እስካለ ድረስ ወደ አገር ላለመመለስ የወሰኑና የማይፈልጉ በውጭ ተሸሽገው በቅጥረኝነት በመስራት ላይ የሚገኙ ቅጥረኛ ባንዳዎች ናቸው በስም የሚታወቁ በመሆናቸው እዚህ ላይ መዘርዘር አይስፈልግም

ነገር ግን እነርሱ ነጋ ጠባ በሚረጩት የፕሮፓጋንዳ መርዝ ምክንያት እኛ መጨቃጨቅ አየገባንም! በጋራ ያለን አገር አንድ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤አሁን ያለው ሁኔታ ጠላቶች በሚሰጡት አጀንዳ በመጠለፍ የአዲሱን ትውልድ ሁለተኛ አድዋ ታላቁን የህዳሴ ግድባችንን እንድንዘነጋ የሚያደርግ ነው ጠላት መዘናጋታችንን ይፈልጋል

ጠላቶች አዲሱ ትውልድ የራሱ አድዋ እንዳይኖረው ሌት ተቀን በመስራት ላይ እንደሚገኙ እያወቅን መጨቃጨቅ የሚጠቅመው የኢትዮጵያችንን ጠላቶች እንደሆነ በመገንዘብ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል መልካም የአድዋ በዓል ይሁንልን!






Post a Comment

0 Comments