የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል



የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው  በስብሰባው  በተለያዩ ሀገራዊ፣ ፓርቲያዊ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ  ይጠበቃል።

በተጨማሪም  ወቅታዊ የሆኑ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር የኢትዮጵያን ብልፅግና በህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማረጋገጥ የሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የሚመክር ይሆናል ነው የተባለው።

ስብሰባው በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ትናንት የተጀመረው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ አስመልክቶ እስከ አሁን ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ተጨባጭ መረጃ ባይሰጥም አንዳንድ ዩቱበሮች ከውስጥ አገኘን በሚል አንዳንድ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎች በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ በዋናነት የፓርቲውን ስብሰባ ሂደት መረጃ በማቅውረብ ላይ የሚገኘው ደረጀ ሃብተወልድ የሚባል ጽንፈኛ ዩቱበር ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ብልጽግና  አመራሮችን"አገሪቱ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለችበት ወቅት በማይሆን አካሄድ ውስጥ ትገኛላችሁ"በማለት ተናግሯቸዋል ሲል ዘግቧል

ይህም በአመራሩ መካከል ልዩነት እንዲፈጠርና በተለይም የኦሮሞና አማራ ህዝብ እንዲጋጭ በመደረግ ላይ የሚገኝ ከንቱ ጥረት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል!

Post a Comment

0 Comments