አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
በዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም በ11ዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው “ አስቸኳይ ” የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ ?
ከዚህም በተጨማሪ ተገልጋዮች ሊገለገሉ ሌሊት ላይ በሚመጡበት ወቅት በተለያዩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የሚደርስባቸው እንግልትና ጉዳት በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋዩ ላይ ተግዳሮት በመፍጠሩ እንደሆነ አገልግሎቱ ጠቁሟል።
ስለሆነም የማስተናገድ አቅም እና ሌሎች ክፍተቶች እስከሚስተካከሉ ድረስ ይሰጥ የነበረው የአስቸኳይ ፓስፖርት መስጠት አገልግሎት መቋረጥ ግድ ሆኗል ብሏል።
አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው በምን ይስተናገዳሉ ?
ቀድሞ ይሰራበት በነበረው አሰራር መሰረት አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው አገልግሎት ጠያቂዎች ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው በዋና መስሪያ ቤት ብቻ ከመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይስተናገዳሉ።
ማሳሰቢያ ፦ ተገልጋዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከህገወጥ ደላሎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የመደበኛ ፓስፖርትን በተመለከተስ ?
የመደበኛ ፓስፖርት ተገልጋዮች ቀድሞ በነበረው ሂደት መስተናገድ #ይቀጥላሉ።
ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
0 Comments