የአማራ ጽንፈኞችን እያሳበደ ያለው እውነት

 

 

 



ፊንፊኔ #Ethiopia የካቲት 24,2015(YMN) ሁሉም እንደሚያውቀው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በርካታ ክፍለ ከተሞች ያለው የሸገር ከተማ መስተዳድር ተመስርቶ ወደ መደበኛ ስራ ገብቷል

ሸገር ከተማ መስተዳድር በመሬት ይዞታ ስፋቱም ሆነ በክፍለ ከተሞች ብዛት ከፊንፊኔ ይበልጣል በተለይም የመሬት ይዞታው ስፋት ከፊንፊኔ በእጥፍ የሚበልጥ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ ከክፍለ ከተማ አደረጃጀት ጋር ተያይዞም በአንድ ክፍለ ከተማ ሸገር ፊንፊኔን በመብለጥ 12 ክፍለ ከተሞች አለው ፊንፊኔ በቅርቡ የተመሰረተውን ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማን ጨምሮ 11 ክፍለ ከተሞች እንዳሏት ይታወቃል

ታዲያ በውጭም ሆነ በውስጥ የሚገኝ ትልቀም ሆነ ትንሽ የአማራ ፅንፈኞችን አንገብግቦ እያሳበደ ያለው ጉዳይ ምንድነው?ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ጽንፈኞቹ መንግስትን ለመገልበጥ የማይሳካ ተደጋጋሚ ሙከራ ለማድረግ የተገደዱት በሸገር ከተማ መስተዳድር ምክንያት እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል

እነዚህ ኃይሎች ከአሁን በኋለ ፊንፊኔን “በረራ”እያሉ የበከተ ፖለቲካቸውን መስራት የሚችሉበት ሁኔታ የለም እንደከዚህ በፊቱ በፊንፊኔ/አዲስ አበባና አካባቢዋ ያለውን የመሬት ሃብት በመውረር ቸብችበው ሚሊዬነር መሆን የሚችሉበት በር ተከርችሞ ተዘግቷል ይህን እውነት በደንብ ስለሚያውቁ ማበዳቸው የሚያስገርም አይሆንም ለማንኛውም ስለ ሸገር ከተማ መስተዳድር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ቢቢሲ አማርኛ የፃፈውን እውነተኛ መረጃ ለማወቅ ያንብቡ https://www.bbc.com/amharic/articles/c51pxx7l12zo

Post a Comment

0 Comments