የብዙ የዓለም ሀገራት ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነዉ ማለት ይቻላል።ዛሬ የዓለም ካርታ ላይ ከምናዉቃቸዉ ሀገራት በርካቶቹ የረጅም ዓመታት ጦርነት ዉጤት ናችዉ። ዘመናዊው የዓለም ታሪክና ትርክት ደግሞ የትላንቱን ጦር ቀስቃሾችን በማንገስና በመዉቀስ ዝሪያ የተቃኙ ሆኖ እናገኘዋለን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለዚህ ሞደል ሀገር ነች ማለት ይቻላል። በታሪክ ጉዳይ ላይ ሁለት ትላልቅ ጎራዎች እንዳሉ ይታወቃል።
በአንድ በኩል የትላንቱን ጦር ቀስቀሾች ጀግና በማድረግና በማንገስ፣ የዋጁትን ጦርነቶች እንደ ብሔራዊ የዓመት በኃል እያከበሩ፣ ለቀስቃሾቹ ደግሞ ሀዉልት እየተከሉ፣ የልደትና የሙት ዓመታቸዉን እያከበሩና እየዘከሩ፣ የጦርነቱ ዉጤት የሆነዉን ሀገርና ድንበር ጠብቆ ማስቀጠል ብቻ እላማቸዉ ያደርጋሉ ናቸዉ። ይሄ ጎራ ለሀገረ መንግሰት እንጅ ለሀገር ግንባታ ዴንታ የሌለዉ፣ ከነሱ መንገድ ያፈነገጠዉን ሁሉ እንደመጤ፣ ያልነቃ፣ የሀገር ስሜት የሌለዉ አድርገዉ የሚከሱ የማንነት መታወቅያ ሰጪዎች ሆነዉ ይገኛሉ። አንድ ሰዉ ኢትዮጵያዊ የሚሆነዉ በነሱ ፍቃድ ብቻ ይመስላቸዋል።
በሌላ በኩል ደግም ያለፈዉ ታሪክ ተበዳይ ሆኖ ራሱን የሳለና የትላነቱን ጦር ቀስቃሾች በመዉቀስና በመክሰስ ላይ ብቻ የተጠመደ ጎራ አለ። ይሄ ጎራ ማንነትን የበደሉ መነሻም፣ የመሰባሰቢያና የነፃነት ትግል መነሻም አድርገዉ ያያሉ። በኢትዮጵያ በርካታ የብሔርተኝነት እንቀእስቃሰዎች የተቃኙት በዚግ መንገድ ነዉ። ሰለዚህ የትላንቱን ጦር ቀስቃሾች አጥብቆ የሚቃወሙ፣ የሚተቹና የሚያንቋሸሹ እንደ ጀግናና ጥሩ ብሔርተኛ መታየታቸዉ የተለመደ ነዉ።
ከላይ እንዳነሳሁት ይሄ የበርካታ ሀገራት ታሪክ ነዉ። ሆኖም ግን በብዙ ሀገራት ሁለቱ ጎራዎች የየራሳቸዉን የታሪክ አተያይ ወደ ጤረጰዛ በማምጣት እንደመደራደሪያ ተጠቅመዉ ተደራድረዉበት፣ ተመካክረዉበት በሰቶ መቀበል ህግ ዘግተዉ ወደፊት ሄዱ። በኛ ሀገር ግን ሰቶ መቀበል የሚባል መርህ ገና ስላልደረሰ ይመስለኛል ሁሉም መቶ ፐርሰንት አሸናፍ ለመሆን ነገሩ በረገጠበት ቆሞ ይገኛል። ትንሽ የረገበ ከመሰለ በኃላ አሁንም እንደ አዲስ እያገረሸ ይመስላል።
አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ የዕዉቀት መለኪያ፣ የምሁርነት መገለጫ፣ የልሂቅነት ማሳያ ሌላኛዉን ጎራ ለመተቸት፣ ለማንቋሸሽ፣ ለማብሸቅ የሚንጠቀማቸዉ የቃላት ጥንካረ የሆነ ይመስላል። “ልክ ልካቸዉን ነገራቸዉ” ለመባል መላላጡ እንደ ሀገር ዋጋ እያስከፈለን መሆኑን የተረዳን አይመስልም። ከዚያ በተጨማር ደግሞ በአዲስ መልክ የተጀመረች “እናተ በኦሮሚኛ እንድህ ብላ ተርታ ነበር” በማለት የብሔር አባልነታቸዉን የጥላቻ መርዛቸዉን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለመዝራት የሚጠቀሙበትን የግል ቂም ሸቃጮችን አምርረን መታገል ያስፈልጋል።
ታድያ መፍቴሄው ምንድነዉ?
በርካታ ሀገረ መንግስታት የጦርነት ዉጤት ብሆኑም የሀገር ግንባታ ሂደት ግን ሁሌም የንግግርና የስምምነት ዉጤት ነዉ። ሰለዚህ በስልጣን ጥማት የታወረ ኢጎን ሰከን አድርጎ በምክንያት ላይ የተመሰረተ ንግግር መጀመር ለኢትዮጵያ እጅግ ያስፈልጋታል። ራስን ብቻ ከማዳመጥ አድገን ሌሎችንም ማዳመጥ፣ ባለሀገር እኛ ብቻ ነን ከሚለዉ የታወረ አስተሳሰብ ተሻግረን ስለጋራ ሀገር መነጋገር፣ እኛ የለንበትም ከሚለዉ ሁሉን ነገር የመካድ ፖለቲካ አልፈን ታሪካዊ ስህተቶችንም ሆነ ጥንካሬዎችን ለመጋራት መዘጋጀት አብሮ ወደፊት ለመሄድ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸዉ።
በዶ/ር ብርሃኑ መገርሳ ሌንጂሶ
0 Comments